Directorates

ማህበራዊ ጥበቃ መከታተያና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

Directorate Director

አቶ መሃመድ ከማል

image description

የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባሪያና መከታተያ ዳይሬክቶሬት  የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓትን በማጠናከር የነዋሪዎች ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና ዋስትና የሚሻሻልባቸውና የሚጠበቁባቸው አሰራር ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤  የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አቀፍ የተሀድሶ አገልገሎት እንዲታቀፍ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤  የከፋ የምግብ ችግር ያለባቸው ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአዕምሮ ህመምተኞች እና መሰል የህብረተሰብ ክፍልች ይለያሉ፣ ይመዘግባሉ፣ለምገባ ኤጀንሲ መረጃውን ያስተላልፋል፤  የምገባ ኤጀንሲ ተጠቃሚዎችን ሁኔታ ክትትል በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ የተቋቋሙት ከምገባ ፕሮግራሙ እንዱወጡ ዝርዝራቸውን ለኤጀንሲ ያስተላልፋል፤  በዘላቂ ማረፍያ የሚፈፀሙ የባይተዋር ቀብሮችን መረጃ ይይዛል፤ ያጠናቅራል፤ የቀብር ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤በበጎ አድራጎት ማህበር ወይም ድርጅት ውስጥ ቆይተው በሞት የተለዩ እና የባይተዋር ቀብር ያስፈፅማል፤  በከተማው ውስጥ ያለ መሠረታዊ እድር እና በየደረጃው የሚገኙት የእድር ምክር ቤቶችን ይመዘግባል፤ ፍቃድ ይሰጣል፤ ባህላዊና ታሪካዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዱሄደ ድጋፍ ያደርጋል፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ያበረታታል፤ የማህበራዊ ጥበቃን መሰረት ያደረገ 1. የማህበረሰብ ክብካቤ ጥምረቶችን በማቋቋም የማበራዊ ችግር ተጎጂዎችን እና ተጋላጮችን ከማህበሰረብ ክብካቤ ጥምረቶች ጋር ማገናኘት 2. የእድሮችን ምዝገባ እና እድሳት አገልግሎት መስጠት 3. የከፋ ምግብ ችግር ተጋላጮችን በመለየት ከምገባ ኤጀንሲ ጋር ማገናኘት 4. የባይተዋር ዜጎችን የመቃብር አገልግሎት መስጠት 5. የስደት ተመላሾችን መረጃ በማጠናቀር ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት ጋር ማገናኘት ናቸው..

Directorate Director's Message

የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባሪያና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የተቋቋመበት ዓላማ፡- በቢሮው ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን በመዘርጋት፣ የእድሮችን የምዝገባ እና እድሳት አገልግሎት በመስጠት ማህበረሰቡን ማህበራዊ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንዲሁም ቀባሪ ያጡ የባይተዋር ሰዎችን ከሆስፒታሎች በመቀበል የቀብር አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የከፋ የምግብ ችግር ያለባቸውን ዜጎች በመመልመል ለምገባ ኤጀንሲ በማስተላለፍ በቀን አንድ ጊዜ ጥራቱን የጠበቀ ምግብ እንዲያገኙ ማድረግና መስራት የሚችሉትን የስነ ልቦና ድጋፍ በማድረግ መስራት የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ድጋፍ ማድረግን ይጨምራል፡፡

Service under the directorate::

Nothing was found.