ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ የተቋማቶቻችን ተቀዳሚ...

image description
- In ሴቶች    0

ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ የተቋማቶቻችን ተቀዳሚ መዳረሻ! ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ

ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ የተቋማቶቻችን ተቀዳሚ መዳረሻ!
ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
ቢሮው በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ማዕከላትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ ያለመ የመስክ ጉብኝት በማካሄድ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ጉብኝቱ ቢሮው በማዕከላቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀጥታ በታዳጊዎች፣ በአረጋውያን፣ በአካል ጉዳተኞች እና በተለያዩ አስቸጋሪ የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ላሉ ማሕበረሰብ ክፍሎች የሚሰጥ አገልግሎቶች በመሆኑ ቅድሚያ መሰጠቱን ገልፀዋል።
በመስክ ምልከታውም በዋናነት የምድረ ግቢን ማዘመን ፣የአረንጓዴ ልማት፣ የከተማ ግብርና ከማስፋፋት አኳያ እንዲሁም የተጀመሩ የግንባታ፣ የእድሳት እና የማዘመን ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የተመላከተ ሲሆን
የተቋማት ተገልጋዮችም ከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ቢሮው የሚያደርገውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በውጤት በመቀየር ለሀገር እና ለወገን ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የአደራ መልዕክት በማስተላለፍ
ቀጣይም የተጀመሩና መሠራት በሚገባቸው ላይ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሊሰሩ የሚገባቸው ተግባራት ላይ በመወያየት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተለይተው እንዲቀርቡና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት ላይ የስትራቴጂክ ካውንስል ጋር በጋራ እንደሚመክሩበትም አሳውቀዋል።
ማዕከላቱ በበኩላቸው ስራዎቻቸው ሰው ላይ የሚሰሩ በመሆናቸው ጉብኝቱ ችግሮች ላይ ለመግባባት ወሳኝ መሆኑን በቀጣይ ከበጀትና ማዕከላቱን ከማዘመን አንፃር ቢሮው ሊያግዛቸው እንደሚገባ ሃሳባቸውን አቅርበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments