ከምገባ ባሻገር ! ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
ከምገባ ባሻገር !
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣን እናኃላፊነት መሰረት ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካልጉዳተኞችን፣ አረጋውያንን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለማህበራዊ እክል የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመደገፍ፣ የመንከባከብ እና መብታቸውን የማስከበር ትልቅ ኃላፊነት ተሸክሞ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በተዘረጋው መዋቅሩ አማካኝነት ልዩ ልዩ አመርቂተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ ይታወቃል።
በዛሬውም ዕለት ከቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር በመሆን በዓለም ለ36ኛ በሀገራችን ለ35ኛ ጊዜ "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት አረጋውያን መልካም ሕይወት" በሚል መሪ ቃል የአረጋውያን ቀንን በማሰብ በክፍለ ከተማው ካሉ የምገባ ማዕከላት የመስራት አቅሙ ላላቸው ባሉበት ቦታ ለመስራት የሚያገለግላቸው ሀይል ቆጣቢ የመስሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማሕበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር የአረጋውያንን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መብትንና ዘላቂነት ያለው ደሕንነቱ የተጠበቀ ክብካቤ እንዲያገኙ አስተዋፅዎ ማድረግ ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
አክለውም በከተማ አስተዳደሩ አቅጣጫ መስራት የሚችሉና አቅሙ ያላቸውን የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ከምገባ ባሻገር ተጠቃሚዎችን በመመልመል የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ያለ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መዓዛ መንግስቱ በበኩላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በታመነባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ በአረጋውያን፣ በሴቶች፣ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ዙሪያ መንግስት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው አረጋውያን በመስሪያ ጊዜያቸው ደምና አጥንታቸውን ገብረው እዚህ ለመድረሳችን ትልቅ ሚና መጫወታቸውን ገልፀው ይሄን ክብራቸውን የሚመጥን ልንልላቸው የሚገቡ ድጋፎችን ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በቀጣይም አስተዳደራቸው አረጋውያን ያላቸውን አቅም ለሃገር እንዲያውሉ በመመካከርና መሰል ተግባራት ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ ከጎናቸውን እንደሆነና በጋራ የመስራት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ አረጋውያን ፕሬዝደንት አቶ እናውጋው መላኩ አረጋውያን የአገር ባለውለታ መሆናቸውን እና ለሀገራቸው ያደረጉትን አስተዋጥኦ በመረዳት መንግስት ትኩረት በመስጠቱ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑንና መብትና ተሳትፏቸው እየጨመረ መሄዱን ጠቁመው አረጋውያንም በቀሪው ጊዘያቸው ለሀገራቨው አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ ፕሮግራሙ እንዲሳካ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በምገባ ማዕከሉ ላይ አገልግሎት ሲያገኙ የቆዩና አቅማቸውን በማሣደግና በማጎልበት ራሳቸውን ችለው ተቋቁመው መስራት እንዲችሉ ለማድረግ ተጠቃሚዎች የእንጀራ ምጣድ፣ የቺፕስ ማሽን፣ የዳቦ መጋገሪያ ምጣድና 25 ኪሎ ዱቄት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
በዕለቱ ወ/ሮ ገነት ቅጣው የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማሕበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ፣ የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ፣ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አመራሮቻቸው በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው አስተዋፅኦ ላደረጉ አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት በዓሉን ከአረጋውያን ጋር በጋራ አክብረዋል
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments