ክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን መልካም ሕይወት! ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
ክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን መልካም ሕይወት!
ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዓለም ለ36ኛ በሀገራችን ለ35ኛ ጊዜ "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን መልካም ሕይወት" በሚል መሪ ቃል የሚከበር የአለም አቀፍ አረጋውያን ቀንን አስመልክቶ በተካሄደ የፓናል ውይይት የአረጋውያንን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መብትን ለማረጋገጥ ወቅቱን ያገናዘበና ምላሸ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።
በቢሮው የማሕበራዊ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣውባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አረጋውያን ብዙ እንክብካቤና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በማመን ቢሮው ለመብታቸው መከበር፣ ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን በመግለፅ በእያንዳንዱ ጉዳይ ተሳትፏቸውና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ከጎናቸው ልንሆን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት ሁሉም የልማት ተግባራት አረጋውያንን ታሳቢ ያደረገ በማድረግ በልዩ ትኩረት የአረጋውያንን ክብርንና አስተዋፅኦ የሚመጥ ልማት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ዘንድሮ የሚከበረው የአረጋውያን ቀንን በዓለም ለ36ኛ በሀገራችን ለ35ኛ ጊዜ የሚከበር መሆኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ ፓናል ውይይት መሆኑንና በዚህም የአረጋውያንን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መብትን ለማረጋገጥ ወቅቱን ያገናዘበና ምላሸ መስጠት እንደሚገባ በመግለፅ ከፓናል ውይይቱ ወቅቱን ያገናዘበና ጉድለቶችን ላይ መፍትሄ አዘል ሃሳቦች የሚጠበቁ መሆኑን አሳስበዋል።
አቶ ጌታቸው ክፍሉ የኢትዬጵያና የአዲስ አበባ አረጋውያን ማህበር ፕሬዝደንት በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ማሕበራቸው አረጋውያን በሚመለከቱ ጉዳዬች ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን በተለይ የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን የተሰሩ ስራዎች በርካታ ተጨባጭ ለውጦችን ለማምጣት እንዳስቻላቸው ገለፀው
በቀጣይም ለአረጋውያን ከተጠቃሚነታቸው አንፃር ዘላቂና ተግባራዊ ምላሽ እንዲሰጥ እንደ ማህበር ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አጋግጠው መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከሴቶችና ማሕበራዊ ሚኒስቴር ተወክለው የተገኙት አቶ ይትባረክ አበበ በበኩላቸው የአረጋውያን ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ መንግስት ለአረጋውያን በሰጠው ትኩረት ውጤቶች መመዝገባቸውን በተለይ በአረጋውያን ዙሪያ የተዛቡ አመለካከቶች መቀረፉቸውን፣ በማሕበር ተደራጅተው መብታቸውን ለማስጠበቅ መንቀሳቀስ መጀመራቸው፣ አለም አቀፍ ስምምነቶችና ሕጎች ወደ ሃገራችን ሁኔታ ተቀይረው መተግበራቸው እና አሰራሮች አረጋውያንን ታሳቢ እንዲያደርጉ መደረጉ መሳያ መሆናቸውን ገልፀው፤
አሁንም አላሰራ ያሉ ህጎች እንዲሻሻሉ ተጠንተው ለውሳኔ የቀረቡ መሆኑን እና በቀጣይም ለአረጋውያን የሚደረጉ ድጋፎች አስገዳጅ እንዲሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለይም ከአዲስ አበባ ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ እና ከአረጋውያን ማሕበር ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አረጋጠዋል።
በእለቱ አቶ ጌታቸው ክፍሉ የኢትዬጵያና የአዲስ አበባ አረጋውያን ማህበር ፕሬዝደንት፣ አቶአማን ዋቢ ከሄልፕ ኤጅ ኢትዬጵያ፣ ወ/ሮ ሜሮን በእውቀቱ ከሕብረተሰብ ተሳትፎና ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ወ/ሮ ሔለን አዱኛ ጤና ቢሮ እና አቶ መኩሪያ መኳንንት በአወያይነት ፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከአረጋውያን ዙሪያ እየተሰሩ ባሉ ጉዳዬች፣ ተግዳሮቶቾ እና በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው ጉዳዬች ዙሪያ በመመካከር የመፍትሔ ሃሳቦችን ጠቁመዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ ከአዲስ አበባ አረጋውያን ማህበር፣ ከሴቶችና ማሕበራዊ ሚኒስቴር፣ አረጋውያን ዙሪያ ከሚሰሩ ከመንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ ከሕብረተሰብ ተሳትፎና ማስተባበሪያ ቢሮ እና በቢሮው የአካል ጉዳተኞች አረጋውያን እና ቤተሰብ ጉዳዬች ማስተባበሪያ ዳሬክቶሬት እና በስሩ የሚያስተባብሩ የሁሉም ክ/ከተሞች ቡድን መሪዎች ተገኝተው ለአረጋውያን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በመግባባት ፓናል ውይይቱ ተጠናቋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments