ቢሮው  የአገልግሎት አሰጣጡን በተቀላጠፈ መልኩ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው  የአገልግሎት አሰጣጡን በተቀላጠፈ መልኩ ለመከወን ለቅንጅታዊ አሰራሮች  ምቹ  ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባው ተገለፀ። ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም  አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

ቢሮው  የአገልግሎት አሰጣጡን በተቀላጠፈ መልኩ ለመከወን ለቅንጅታዊ አሰራሮች  ምቹ  ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባው ተገለፀ።

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም  አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና  ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር የአገልግሎት አሰጣጡንና ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን በሚረዱ የአሰራር ሂደቶች ዙሪያ ምልከታ  አካሄደ፡፡

በዕለቱ የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ  የቢሮውን  ተቋማዊ አሰራርን ለማሻሻል ያለመ  ንቅናቄ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ይሄንኑ ንቅናቄ ከግብ ለማድረስ ይረዳ ዘንድ በከተማችን ካሉ ቢሮዎች በተከታታይ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከሚታወቀው የትምህርት ቢሮ ጋር ልምድ በመካፈል

ቢሮው  ካለው የውስጥ  አቅም እና ክህሎት ጋር  አጣምሮ በመቀጠል ጥንካሬን ለማስቀጠል የታዩ ክፍተቶቻችን ለማረም ደሞ በምን መንገድ ብንሄድ ችግሮቹን አልፈን እንሻገራለን የሚለውን ልምድ ለማግኘት ያለመ ምልከታ መሆኑ አብራርተዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላት በበኩላቸው ቢሯቸው እዚህ ለመድረስ በርካታ ውጣ-ውረዶች እንዳለፈ፣ ተከታታይነት ያለው የአመለካከት ቀረፃ ስራ መሰራቱን ከታች ከወረዳና ከት/ቤት ጀምሮ ወደ ላይ የለውጥ እሳቤ እንዲሰፍን ጥረት መደረጉን፣ ስራው የእኛ ነው የሚል መንፈስ እንዲሰፍን ጥረት መደረጉን፣ በተከታታይ ወጥ አሰራሮች መተግበራቸው፣ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማስቻሉን ገልፀዋል።

በዕለቱ በዋናነት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ ተግባራት ክትትልና ድጋፍ አሰራር፣ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የሚተገበሩ ተግባራት እንዲሁም አሰራሮችን ለማዘመን እና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በተጨባጭ ተዳሰዋል።

በተጨማሪም ቢሮው የደረሰበት የስኬት ደረጃ ለመድረስ አስተዋፅኦ ያደረጉ አሰራሮች፣ የስራ ባህሎች ወደ ሰራተኛው የተስፋፋበት፣ መረጃዎች የተደራጁበት እና ታችኛው መዋቅር ድረስ የወረደበትን አግባብ ላይ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን

በቀጣይም  ሳይንሳዊ አሰራሮች በተግባር እንዴት እየተተገበሩ መሆኑ ለመረዳት ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው፣ የሚታይ፣ የሚጨበጥ ሥራዎች መመልከታቸውን በቀጣይ ወስደው ለማስፋት ጥሩ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments