አዲሱ አዋጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር ያካተታቸው ተግባራት!
አዲሱ አዋጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር ያካተታቸው ተግባራት!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የመንግስት ምስረታ እና 4ኛ ዙር የምክር ቤት ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት እንደተገለፅው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲካታተት ማፅደቁ ይታወቃል።
በእዚህም ቢሮው በምክር ቤቱ በአዋጅ የፀደቁ እና ወደ ቢሮው የተካተቱ ተግባራትን በፍጥትነ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ ጋር በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለፁት ወደ ቢሮው የተካተቱ ተግባራት የማህበራዊ እክል ተጎጂ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እፎይታን የፈጠረ ብሎም የብዙዎችንም ተስፋ ያለመለመ በመሆኑ ይህንኑ አገልግሎት ወጥ ና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
በመሆኑም ይህንኑ ተግባር ለማስቀጠል እና በፍጥነት ወደስራ ለማስገባት በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ኮሚቴ በማዋቀርም ወደ ስራ ተገብቷል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments