"የአገልግሎት አሰጣጣችን የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ያለመ ሊሆን ይገባል” የሕፃናት ማህበራዊ ጉዳይ እና ሴቶች ቢሮ ኃላፊ
"የአገልግሎት አሰጣጣችን የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ያለመ ሊሆን ይገባል”
የሕፃናት ማህበራዊ ጉዳይ እና ሴቶች ቢሮ ኃላፊ
ወ/ሮ ልእልት ግደይ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ በተሰጡ ሹመቶች መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት በወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም አዲስ ተሹመው በመጡት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ መካከል የስራ ርክክብ እንደተደረገ የሚታወስ ነው።
በዛሬውም ዕለት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በልዩ ልዩ የስራ ሂደቶች ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀ ምክክር ላይ እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጣችን የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ያለመ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ስራቸውን በይፋየጀመሩት ኃላፊዋ አክለውም የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሳደግ የቢሮው ተቀዳሚ ተግባር ለማድረግ በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የዕለቱ ተሳታፊዎችም የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments