የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የቢሮው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ቅብብሎሽ!
የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የቢሮው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ቅብብሎሽ!
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ በተሰጡ ሹመቶች መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም አዲስ ተሹመው በመጡት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ መካከል በዛሬው እለት የስራ ርክክብ ተደርጓል።
የቢሮው ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በቢሮው የሚተገበሩ ሰው ተኮር ስራዎች እና እየተሰሩ ያሉትን፣ ጅምር ስራዎች እንዲሁም የቢሮው አሁናዊ ሁኔታ ገለፃ በማድረግ በቀጣይም ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር በጋራ በመተጋገዝ መከናወን ባለባቸዉ ተግባራት ላይም ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።
አዲስ የቢሮው ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው ቢሮው የሚሰራቸውን ስራዎች በበርካታ የስራ አጋጣሚዎች እንደሚረዱት ጠቅሰው በቀጣይም ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር በአንድ መንፈስ ተግባብተንና ተስማምተን በጥሩ የስራ መንፈስ ጥሩ ዉጤት ማምጣት እንደሚጠበቅ እና ለዚህም ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ቢሮው የቢሮው ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ለነበራቸው የስራ ቆይታ እያመሰገነ አዲስ ተሹመው ለመጡት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል።
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments