በሰው ተኮር አሰራር የተመዘገቡ ስኬቶች! ነሀሴ...

image description
- In ሴቶች    0

በሰው ተኮር አሰራር የተመዘገቡ ስኬቶች! ነሀሴ 01 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

በሰው ተኮር አሰራር የተመዘገቡ ስኬቶች!

ነሀሴ 01 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣን እናኃላፊነት መሰረት ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካልጉዳተኞችን፣ አረጋውያንን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለማህበራዊ እክል የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመደገፍ፣ የመንከባከብ እና መብታቸውን የማስከበር ትልቅ ኃላፊነት ተሸክሞ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በተዘረጋው መዋቅሩ አማካኝነት ልዩ ልዩ አመርቂተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ ይታወቃል።

ይህ ስራ የአንድ ጊዜ ወይም የተወሰነ ወቅት ስራ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው፣ በየእለቱ የሚከናወን እና ልዩ ትኩረት፣ቅንጅት እና ቁርጠኝነት የሚሻ ተግባር ነው።

በተለይም ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አንስቶ እስከ ቀጥተኛ ድጋፍ አሰጣጥ፣ ከፖሊሲ ትግበራ አንስቶ እስከ መስክ ክትትል እና ድጋፍ ድረስ ያሉትን በርካታ ስራዎች በቢሮ ደረጃ፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ በሚገኙ መዋቅሮች አማካኝነት ሲተገብር ቆይቷል፤ አሁንም እየተገበረ ይገኛል። ለመጥቀስ ያክልም፤

በ2018 በጀት ዓመት

👉🏽 ሕፃናትን መብት፣ ተሳትፎና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማስጠበቅ የአመለካከት ለውጥ ሊያመጡ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች፣ የአመለካከት እና የክህሎት ስልጠናዎች በመስጠት የከተማው ህብረተሰብ ግንዛቤ አድጓል፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ በርካታ ሕፃናት በአማራጭ የሕፃናት ክብካቤ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

👉🏽በቀዳማዊ ልጅነት እድገት ፕሮግራም ሕፃናት በየወሩ የአልሚ ምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ህፃናት ጤናማ እድገት እንዲኖራቸው አስችሏል፤

👉🏽የሕፃናት ማቆያ ማዕከላትን በማቋቋም ናበማጠናከር እና ምቹ የመጫወቻ ስፍራዎችን በማስፋፋት ሕፃናቶች እንዲጫወቱ እና በቀን ማቆያ ስፍራዎች እንክብካቤ እያገኙ እንዲውሉ በማድረግ ደስተኛ ሆነው እንዲያድጉ እንዲሁም ከተማችን አዲስ አበባ ሕፃናትንለማሳደግ ምርጧ ከተማ ለማድረግ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

👉🏽የሴቶችን መብት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች፣ የአመለካከት እና የክህሎት ስልጠናዎች ለከተማዋ ሴቶች፣ ሴት አደረጃጀቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች በመስጠት አቅማቸውን ማጎልበት ተችሏል፤ እንዲሁም

👉🏽 በሴቶች ዘንድ የነበረውን የተሳሳተ የስራ ባህል በመቀየርና ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች/ መስኮች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል፤ በተጨማሪም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በሰላምና ፀጥታ እና በመሳሰሉት ሃገራዊ ጉዳዮች ያላቸው ተሳትፎ አድጓል።

👉🏽የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲን ለማስተግበር በህብረተሰቡ ዘንድ የአመለካከት ለውጥ ሊያመጡ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመፍጠር፣ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን በመዘርጋትና አገልግሎቶችን በማስፋፋት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት፣ የሲቪል እናየሲቪክ ተቋማትን በማጠናከር፣ እድሮችና መሰል አደረጃጀቶች ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን በመደገፍ ችግራቸው ማቃለል ተችሏል፤

👉🏽በተጨማሪም አካልጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማሳደግ ራሳቸውን በገቢ እንዲደግፉ ተደርጓል።
በእነኚህና ሌሎች ውጤቶች የተገኙት በአንድአካል ጥረት ብቻ አይደለም። ከከተማ አስተዳደሩ ጀምሮ የቢሮው የበላይ አመራር እና ጠቅላላ ሰራተኞች እስከ ከክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች እስከ ወረዳ ፈፃሚዎች ጋር በተደረገ የተቀናጀ እና የተናበበ ጥረት የተመዘገበ ውጤት ነው።

ቢሮው ለተያዘው እቅድ ስኬት ሁሉም የበኩሉንጥረት እያደረገ መሆኑን ያምናል፤ ይህንንም ጥረት በአግባቡ የመመዘን፣ የመለየት እና እውቅና የመስጠት ኃላፊነት እንዳለበት እሙን ነው ።

በዚህ መሰረት ቢሮው በ2018 የበጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዳይሬክቶሬቶች፣ ተቋማት፣ ክ/ከተሞችና ባለሙያዎች የዕውቅና የሽልማት መርሀ ግብር አካሂዷል። በተጨማሪም በቢሮው ለረጅም ጊዜ አገልግለው በጡረታ ለተሸኙ ሰራተኞች የእውቅና ሰርተፍኬትና የክብር ሽኝት ተደርጓል።

ይኸውም ዋናው አላማ ጤናማ የተወዳዳሪነት መንፈስ መፍጠር፣ ተቋማዊ አሰራር ማረጋገጥ እና ክፍተቶች በመለየት በቀጣይ በጀት አመት ልዩ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተብራርቷል።

በመድረኩ የተገኙ አካላትም በእውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብሩ መደሰታቸውን በመግለፅ በቀጣይም ለተሻለ ስራ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments