ብሔራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩል...

image description
- In ሴቶች    0

ብሔራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት ፖሊሲ መፅደቁ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ መሆኑ ተገለፀ። ሐምሌ 10 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

ብሔራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት ፖሊሲ መፅደቁ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ መሆኑ ተገለፀ።

ሐምሌ 10 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በፌዴራል መንግሥት የጸደቀውን "ብሔራዊ የሴቶች ማብቃትና ስርዓተ ፆታ እኩልነት ፖሊሲ" በመዋቅሩ ውስጥ ላሉ እና ለሚመለከታቸው አካላት የትውውቅ እና የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ አካሂዷል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት በቢሮው የሴቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ እንደገለፁት በ1986 ዓ.ም የተቀረፀውና ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፖሊሲ ለሀገራችን ሴቶች መልካም አጋጣሚዎችንና ዕድሎችን የመፍጠሩን ያህል በርካት ክፍተቶች እንደነበሩበት በተካሄደ የግምገማ ጥናት ለመገንዘብ በመቻሉ

ካለፈው ትምህርት በመውሰድ ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ መልኩ ፖሊሲው መፅደቁ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ስልጠናውን በጥብቅ ዲሲፕሊን እና የእኔነት ስሜት መከታተል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በበኩላቸው ፖሊሲው ተጠያቂነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ በቂ ትኩረት የሚሰጥ እንዲሁም ጥበቃና ምላሽ ለመስጠት በፅኑ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ በቢሮው የሴቶች ዘርፍ አማካኝነት ስለ "ብሔራዊ የሴቶች ማብቃትና ስርዓተ ፆታ እኩልነት ፖሊሲ" ዋና ዋና ይዘቶች፣ ዓላማዎችና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች ዝርዝር ገለጻ የቀረበ ሲሆን

በተለይም ፖሊሲው የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፎች ለማሳደግ፣ የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና በተቋማት ውስጥ ተጠያቂነትን ለማጠናከር የሚያግዝ አጠቃላይ ማዕቀፍ መሆኑን ተገልጸዋል።

በተጨማሪም የዕለቱ ሰልጣኞች ፖሊሲው ውጤታማ እንዲሆን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ ትብብርና የጋራ ኃላፊነት እንዲወስዱ መልዕክት ተላልፏል።

በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞች ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዘርፍ አስተባባባሪዎች፣ በቢሮው የሴቶች ዘርፍ ቡድን መሪዎች እና ተወካዮች በፖሊሲው አፈጻጸም ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማካሄድ፣ ቀጣይ ትግበራዎችን የሚያጠናክሩ ገንቢ ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments