ሮው የ90 ቀናት ክንውኖች እንዲሁም ለሕፃናት ም...

image description
- In የኽጻናት    0

ሮው የ90 ቀናት ክንውኖች እንዲሁም ለሕፃናት ምቹ የመዝናኛና የመጫወቻ ቦታዎች ማስተግበሪያ ማንዋልን አስመልክቶ ምክክር አካሄደ። ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ


 ቢሮው የ90 ቀናት ክንውኖች እንዲሁም ለሕፃናት ምቹ የመዝናኛና የመጫወቻ ቦታዎች ማስተግበሪያ ማንዋልን አስመልክቶ ምክክር አካሄደ።

ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ


ቢሮው እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም በሚቆየው በ90 ቀናት እቅዱ ለማከናወን በተዘጋጀ የ500,000 ሴቶች ፣ አረጋዊያን እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲሁም 390,000 ሕፃናትን ለማሳተፍ አላማው ያደረገ የንቅናቄ ዕቅድ ዙሪያ እንደሁም የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የጋራ አድርጎ ወደ ትግበራ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን

በዛሬውም ዕለት የቢሮው የበላይ አመራር፣ ከክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ፣ የዘርፉ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ90 ቀናት የእቅድ አፈፃፀም ሂደትን እንዲሁም ለሕፃናት ምቹ የመዝናኛ ና የመጫወቻ ቦታዎች ማስተግበሪያ ማንዋል ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፥ የቤት ግንባታ፣ የፅዳት ስራዎች፥ የአረጓዴ አሻራ፥ ማዕድ ማጋራት፥ የስራ እድል ፈጠራ ፣ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ፥ ደም ልገሳ፥ ተረጅነትና ድህነት ቅነሳ እንዲሁም ሴቶችን እና ሕፃናትን ከጥቃት የመከላከል ስራዎች የአፈፃፀም ሂደት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በስፋት በመዳሰስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።

በመድረኩ የተገኙት የቢሮው የሴቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ በሁሉም መስክ ውጤታማ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን አረጋግጠው ይሄንኑ ለማስቀጠል እና የሚታዩ የአፈፃፀም ልዩነቶችን ለማስተካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማስቀጠል እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን

የቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በበኩላቸው ተግባራቱ ተቋማዊ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ አጀንዳዎቻችን በመሆናቸው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ በቀጣይም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት መመራት
የሚገባቸው፡-

👉የተጀመሩ የቤቶች ግንባታን ማፋጠን፣
👉ከፍተኛ ሀብት ፈሶባቸው የለሙ ( የሕፃናት የመጫወቻ ቦታዎችን ጨምሮ) ቦታዎች መንከባከብ ፅዳታቸውን መጠበቅ
👉 የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሁሉም ዜጋ ባህል እንዲያደርገዉ የማስቻል ስራ መስራት
👉 ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በልዩ ትኩረት መስራት
👉 ከተረጅነት ለመሸጋገር የተጀመሩ የሰብዓዊ ስራዎች ማስቀጠል እንደሚገባ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን

በተያያዘም ለሕፃናት ምቹ የመዝናኛ ና የመጫወቻ ቦታዎች ማስተግበሪያ ማንዋል ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሚተገበሩ ተግባራት ዙሪያ በስፋት በመወያየት የቀጣይ አካሄዶችን አመላክቷል።
[13-Aug-26 10:58 AM] Beruketawit Biro: [ 8 photos ]


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments