የቀዳማይ ልጅነት ልማት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ግምገማ መድረኩን ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ።
የቀዳማይ ልጅነት ልማት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ግምገማ መድረኩን ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ።
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ልማት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ግምገማ መርሐ-ግብር መድረኩን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ አካሄደ።
በግምገማ መድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ ቢሮው ከተመረጡ የአልሚ ምግብ አቅራቢ የሸማች ሕብረት ስራ ማሕበራት ጋር የ3 ዓመት፣ የአመቱን ዕቅዶች የጋራ ተደርገው ወደ ተግባር መገባቱን እና በየሩብ ዓመቱ አፈፃፀሞች የጋራ ግምገማ እየተደረገባቸው መኬዱን ገልፀው፤ በበጀት ዓመቱ ቢሮው ባሰራጨው የአልሚ ምግብ ስርጭት ላይ በሁሉም ክ/ከተሞች ስርጭቱ ላይ የተሳተፉ ሕ/ሥራ ማሕበራት ሰብአዊነትን በመላበስ ከልብና ከበጎነት አንፃር በመስራታቸው ለተገኘው ጥሩ አፈፃፀም አስተዋፅኦ ማድረጋቸውአብራርተዋል።
የቀዳማይ ልጅነት እድገት ክትትል ዳይሬክቶሬት ከፈተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አንድነት አላምረው የቀጥታ ዓልሚ ምግብ ድጋፍ አላማ ከፅንሰት ጀምሮ እስከ 3 ዓመት ላሉ ህፃናት ለሁለንተናዊ እድገታቸው የሚሆን አስፈላጊውን አልሚ ምግብ በማቅረብ አምራች ዜጋ ማፍራት መሀ
ለግምገማ መድረኩ በአልሚ ምግብ ድጋፍ አገልግሎት የታዩ አፈፃፀሞችን፣ በጥንካሬና በድክመት የታዩ ሪፖርት አቅረብው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የቀዳማይ ልጅነት እድገት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሕይወት ደረሰ በግምገማ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ስራው አድካሚ ነገር ግን ሀገራችን ነገ ለምትፈጠረው ትውልድ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እያደረጋችሁ በመሆኑ ተስፋን እየቀጠልን እንደሆነ በማሰብ ትልቅ ኃላፊነቶችን መወጣችሁ ለዛሬው ስኬት አብቅቶናል፡፡ የአልሚ ምግብ ስረጭት ሃሳብ ነበር ሃሳቡን ወደ ተግባር በመቀየር ሂደት የሸማች ሕብረት ስራ ማሕበራት ከመዋቅራችን ጋር በመናበብ ሰፊ ሚና መጫወታቸውን በግምገማ መድረኩ ከተነሱት በላይ ችግሮችን በመቋቋም እቅዱ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ ተሳታፊ የሸማች ሕብረት ሥራ ማሕበራት ስራውን ሲሰሩ ከተሰጣቸው ኃላፊነት በዘለለ ሀገራዊና ሕዝባዊ አደራዎች አንፃር መሆኑን፣ በየጊዜውም አሰራራቸውን በማረም የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን እና ቅንጅታዊ አሰራሮች መስመር መያዛቸውን ነገር ግን አልፎ አልፎ በተጠቃሚዎች የሚነሱ ፍላጎቶች መጨመርና ሂሳብ ክፍያ መዘግየት አንፃር ሃሳብ ጥያቄ አቅርበው ነገር ግን ቢሮው እድሉ በማመቻቸቱና ተደረሽ ስራዎችን እንዲሰሩ ያደረገበትን አግባብ አመስግነዋል።
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments