የሚዲያ እና የኮሚውኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር ተቋማዊ ብሎም ለሀገራዊ አንድነት ትርክት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ተገለፀ።
የሚዲያ እና የኮሚውኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር ተቋማዊ ብሎም ለሀገራዊ አንድነት ትርክት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ በ2018 በጀት ዓመት የተሰሩ አበይት ሥራዎችን አስመልክቶ ለ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የፎቶ- አውደ ርዕይ ተገልጋዮች፣ የቢሮው ከፍተኛ አመራር፣ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ከፈተ።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት በ2018 ዓ.ም በሁሉም ረገድ አበረታች ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀው እነዚህን ስራዎች ለህዝብ ይፋ በማድረግ ሃሳብና አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑን ገልፀው
አያይዘውም የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የተሟላ የሰው ኃይል እና በቂ ግብዓት ባልተሟላበት በዚህ ደረጃ የተሳካ አውደ-ርዕይ መዘጋጀቱ ሊበረታታ እንደሚገባ በመግለፅ
ለእዚህም የሚዲያ እና የኮሚውኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር ተቋማዊ ብሎም ለሀገራዊ አንድነት ትርክት አስተዋፅኦ የጎላ በመሆኑ ዘርፉን ማበረታታት የሁሉም ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት ወ/ት ብሩክታዊት ምስክር ቢሮው በበጀት አመቱ በእቅድ ይዞ ያከናወናቸውን ተግባራት ለሕዝብና ለባለድርሻ አካላት ግልፀኝነት በመፍጠር ስራዎችን ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ የፎቶ አውደ-ርዕይ መሆኑን ገለፀው
ቢሯችን የማሕበራዊ ፍትህ ዙሪያ የሴቶች፣ ሕፃናትና የመሕበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የእኩል ተሳታፊናትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ተግባራትን በስኬት ማከናወናቸውን እነዚህን ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ የፎቶ አውደ -ርዕይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በፎቶ አውደ-ርዕዩ ላይ ተገኝተው ምልከታ ያደረጉ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ተገልጋዬች በተመለከቱት የፎቶ አወደ-ርዕይ መደሰታቸውን ቢሮው ያከናወናቸውን በርካታ ተግባራት ገላጭ በሆነና ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስቻለ መሆኑን፣ ለበርካታ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ለማሕበራዊ ችግር ተጋለጭ ዜጎች የተሰጡ አገልግሎቶች እና የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶችን በስፋት የተረዱበት መሆኑ ገልፀዋል።
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments