በቢሮው ስር የተቋቋመው የመማክርት ጉባኤ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻሎችን ለመፍጠር ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ። ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
በቢሮው ስር የተቋቋመው የመማክርት ጉባኤ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻሎችን ለመፍጠር ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ።
ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር የተቋቋመው የመማክርት ጉባኤ ከስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ጋር ያደረጉትን የድጋፍና ክትትል አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት።
የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሰመድ ሻሚል በመድረኩ እንደገለፁት የመማክርት ጉባኤ በዚህ ደረጃ የተደራጀ ስራዎች በመስራት እና ክፍተቶችን ለማመላከት እያደረገ ያለው ጥረት ጥሩ መሆኑን ገልፀው በመድረኩ የሚቀርቡ ነጥቦችን ለቅመን ለ2019 በጀት በመነሻነት እንደሚወሰዱ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ቢሮው የትኩረት መስክ እንደሚያደርጋቸው በመጠቆም የመድረኩን የሪፖርት ግምገማ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።
ሪፖርቱን የመማክርት ጉባኤው ሰብሳቢ የሆኑት መቶ አለቃ ጥላዬ ሽፈራው ያቀረቡ ሲሆኑ በተደረገ ክትትልና ድጋፍ የታዩ ክፍተቶች መለየታቸውን ገልፀው ከነዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የተፈቱ ፣ በሂደት ላይ ያሉ እንዲሁም ማብራሪያ ተሰጥቷቸው በቀጣይ የሚታዩ መሆናቸውን ገልፀው
እርምት የሚፈልጉ ተብለው በተነሱ አሰራሮች ዙሪያም ዳይሬክቶሬቱትና በየማዕከላቱ ችግሮቹን ለመቅረፍ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችንና የአመራርና ባለሙያ ቁርጠኝነት በታየባቸው ስኬቶች መመዝገባቸውን እና በቀጣይ ሊፈቱበት የሚችሉባቸውን የተገመገሙ ያሏቸውን አማራጮች አቅርበዋል።
የቢሮው ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዬናሰ ሲሳይ በበኩላቸው የመማክርት ጉባኤው በሚያደርገው ድጋፍና ምክረ-ሃሳብ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡና ውሳኔዎች እየተሰጡ መሆኑን አስረድተው ቢሮው በተገኙ ምክረ ሀሳቦች እድለኛ መሆኑን በቀጣይም 2019 በጀት አመት ተግባራቱ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በሪፖርት ግምገማው መድረኩ ላይ የተሳተፉ የጉባኤው አባላት፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ተወካዮች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ስራ አስኪያጆች ችግሮቹ የተለዩበትን አግባብ አድንቀው ከመቋቋም ከሚገባቸው ተገልጋዬች አንፃር፣ ከተሽከርካሪ አንቡላንስ፣ ከምግብ ግብአት እጥረትና ጥራት አንፃር፣ የተገልጋይ ማደሪያ ክፍሎች አድሳት እና መሰል ጥያቄዎች ለይ በዋነኛነት በመገምገም የቀጣይ የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments