ልጆች ከልብም ይወለዳሉ!

image description
- In የኽጻናት    0

ልጆች ከልብም ይወለዳሉ!

ልጆች ከልብም ይወለዳሉ!

ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን ከተማችን ልጆችን ለማሳደግ ምርጧ እና ተምሳሌታዊ ከተማ መሆኗን ለማረጋገጥ መጠነ ሰፊ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ይሄንኑ ውጤታማነት ለማስቀጠልም በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን በስሩ በሚገኙ ተቋማት ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ እንክብካቤ ከማድረግ በተጨማሪ

አማራጭ የእንክብካቤ መንገዶችን በማመቻቸት አንድ ሕፃን ከወላጁ ጋር መኖር እንደማይችል ወይም የተቋጥሮ ዝምድና ካላቸው የቤተሰብ አባላት ክብካቤን ማግኘት እንደማይችል ለማረጋገጥ ሁሉም ምክንያታዊ ጥረቶች ከተደረጉ በኋላ በአደራ መልክ በጉዲፈቻ ለመልካም እና ልበ ቀና ቤተሰቦች ለሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ ቤተሰቦች የሚያገናኝ ሲሆን

በበጀት ዓመቱ ቢሮው ከ165 በላይ ሕፃናትን በአደራ መልክ ለሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ ለመልካም እና ልበ ቀና ቤተሰቦች ጋር ያገናኘ ሲሆን

በዛሬውም ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንዲሁም የሴቶች ሕፃናት ማሕበራዊ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በተገኙበት ሕፃናቱን ከልበ ቀና ቤተሰቦች ጋር አገናኝቷል።

ቢሮው ጉዲፈቻው በሕፃኑ፣ በወላጆች ወይም በአሳዳጊዎች ወይም በሞግዚት ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመረዳት የሚያስችል ምክር እና ሥልጠና እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል።

 

 

ሰኔ 13 ቀን 2018ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments