ቢሮው በ10.7 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ በማድረግ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው በ10.7 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በከተማዋ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ ስርጭት መርሃ-ግብር አካሄደ። ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

ቢሮው በ10.7 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በከተማዋ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ ስርጭት መርሃ-ግብር አካሄደ።

ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለ150 ሕፃናት እና ለ100 አዋቂ አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ ስርጭት መርሃ-ግብር አካሄደ።

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ድጋፉን የሰጠው ለ100 ሕፃናት እና ለ150 አዋቂዎች መኾኑን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ አስታውቀዋል።

ድጋፉ ትኩረት ያደረገው ለችግር ተጋላጭና ተጎጅ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መኹኑንም ቢሮ ኃላፊዋ ጠቅሰው

አካል ጉዳተኞች በመንቀሳቀሻ እጥረት የተነሳ ቤት ለመዋል ተገደዋል ያሉት ኃላፊዋ የተደረገው ድጋፍ ከቤት ወጥተው በራሳቸው እንዲንቀሳቀሱ ብሎም ውሳኔ ለመወሰን ያስችለዋል ነው ያሉት።

አቶ አለማየሁ ማሞ በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን የጉዳዩ ባለቤት አካል ጉዳተኞች እንደሚያውቁት ገልፀው

ቢሮው የአካል ጉዳተኞች አረጋዊያን እና ቤተሰብ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሕይወት በቀለ ቢሮው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ደጋፊ የሌላቸው የማሕበረሰብ ክፍሎችን በማጥራት ለ150 አካል ጉዳተኛ ሕፃናትና ለ100 አዋቂ አካል ጉዳተኞች በ10.7 ሚሊዬን ብር ዋጋ ወጪ ተደርጎ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በተደረገው ድጋፍ ታዳጊ ሕፃናት ከእናቶቻቸውና ከቅርብ ቤተሰባቸው ጀርባ ወርደው በራሳቸው ተንቀሳቅሰው ወደ

ት/ቤት እንዲሄዱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በአጠቃላይ በድጋፍ ስርጭቱ ተጠቃሚ በሆኑ አካላት ዙሪያ የእኩል ተሳታፊናትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ድጋፍ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዕለቱ የድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑ አካላት ባስተላለፉት መልዕክት ብዙ ጊዜ የሚያያቸው የጠፋበትና ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እየተጋፈጡ የነበረበትን ጊዜ ማሳለፋቸውን አሁን ላይ ችግራቸውን መንግስት አይቶ በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና ቀጣይ ሕይወታቸውን የተሻለ ለማድረግ፣ ልጆቻቸው ካለባቸው የአካል ጉዳት አንፃር የሚደርስባቸውን ተፅእኖ ለመቅረፍ፣ በማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ዙሪያ የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች የሚፈታ መሆኑን ገልፀው ቢሮው ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments