በመስሪያ ቦታ የሚገኙ የሕፃናት የቀን ማቆያ እና...

image description
- In የኽጻናት    0

በመስሪያ ቦታ የሚገኙ የሕፃናት የቀን ማቆያ እና ክብካቤ ማዕከላት ለወላጆች የስራ ምርታማነት እና ለሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በመስሪያ ቦታ የሚገኙ የሕፃናት የቀን ማቆያ እና ክብካቤ ማዕከላት ለወላጆች የስራ ምርታማነት እና ለሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተገለጸ።

 

ቢሮው የክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ኢንሼቲቭ የሆነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን በርካታ ተግባራትን ሲተገብር መቆየቱ ይታወቃል።

የፕሮግራሙ አንድ አካል የሆነው እና በርካታ እናቶች እና ሕፃናትን ተጠቃሚ ያደረገው የመስሪያ ቦታዎች የሕፃናት የቀን ማቆያ እና ክብካቤ ማዕከላት ተጠቃሽ ሲሆን በእነዚህ ማዕከላት ላለፉት 3 እና 4 አመታት ተገቢውን እንክብካቤ ያገኙ ንቁ የሀገር ተረካቢ ሕፃናት የፕሮግራሙን ውጤታማነት በማመላከት ወደ መደበኛ የትምህርት አለም እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።

ቢሮውም በተቋሙ ውስጥ የሚገኘውን የሕፃናት የቀን ማቆያ እና ክብካቤ ማዕከል ቆይታቸውን ጨርሰው የሚወጡ ሕፃናት የምርቃት እና የሽኝት መርሀ-ግብር አካሂዷል።

በዕለቱ የተገኙት የቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም እውን ሆኖ በእዚህ ልክ ፍሬውን መሰብሰቡ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ ፕሮግራሙ እንዲሳካ ከክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ አካላትን የቢሮውን የበላይ አመራር እና የዳይሬክቶሬቱን አባላት እንዲሁም የማዕከሉ አስተባባሪ እና ተንከባካቢ ባለሙያዎችን በቢሮው ስም አመስግነዋል።

በዕለቱ የተገኙ ወላጆችም በመስሪያ ቦታ የሚገኙ የሕፃናት የቀን ማቆያ እና ክብካቤ ማዕከላት (ዴይ ኬር) ሕጻናትን ከመጠበቅ አገልግሎት ባለፈ፣ ለእኛ ለወላጆችም የስራ ምርታማነት እና ለሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ገለፀዋል።

ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments