ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አስመልክቶ ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የግምገማ መድረ አካሄደ። ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አስመልክቶ ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የግምገማ መድረ አካሄደ።
ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አስመልክቶ ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የግምገማ መድረኩን አካሄደ።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በቢሮው የማሕበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ቢሮው በ9 ወራት አመርቂ ሰው ተኮር ሥራዎች የተሰሩበት የቢሮው አመራርና ሰራተኞች ተቀናጅተው በመሥራታቸው ለበርካታ የማሕበራዊ ችግር ተጋላጭ ዜጎችን ችግር መቅረፍ መቻሉን በሂደቱም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ በጋራ በመግባባት በጥሩ አፈፃፀም የቀሩ ሥራዎችም ለማጠናቀቅ ያለመ የግምገማ መድረክ መሆኑን በመግለፅ መድረኩን ከፍተዋል።
በዕለቱም ለቀረቡ ጥያቄዎች ምለሽ በመስጠት የማሕበራዊ ችግር ተጋላጭነታቸው ከፍ ያሉ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንንና አካል ጉዳተኞችን በማገልገል አስተዋፅኦ ላደረጉ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ በማዕከላት የሕፃናት ማቆያዎችን ለማስፋፋት ግብዓቶች መለየታቸውን እና በምዘና አፈፃፀም ለተመዘገቡ ውጤቶች እውቅና ለመስጠት አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሄድበት አስገንዝበዋል።
በቢሮው የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አጥላው ተ/ፃዲቅ የቢሮው ጥቅል አፈፃፀም 97% መሆኑንና በእያንዳንዱ ግብ የዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም፣ በታዩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎችን እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሰመድ ሻሚል በመድረኩ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ የተገኙ ውጤቶች በአመራሩና በሰራተኛው የተሰጠው ትኩረት፣ ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነቶች በመሻሻላቸው የመጣ ውጤት መሆኑን ነገር ግን የታዩ ውስን ክፍተቶች ቢሆኑም ለምን በሚል በመፈተሽ በጉድለቶችና ጥንካሬዎች የጋራ መግባባት በመያዝ ወጥ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።
በግምገማ መድረኩ የተሳተፉ ሰራtኞችም የግምገማ ሪፖረቱ ግልፅ በሆነ መንገድ መቅረቡን፣ ሰራተኛው ላስመዘገበው ስኬት ትኩረት የሰጠ መሆኑን በቀጣይም ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ገልፀው ነገር ግን ከእውቅና አሰጣጥና ከሕፃናት የቀን ማቆያ አንፃር መሻሻል የሚገባቸውን ነጥቦች በማቅረብና በመግባባት መድረኩ ተጠናቋል።

Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments