አረጋዊያን በከተማችን የልማት ጉዞ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ። ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢ
አረጋዊያን በከተማችን የልማት ጉዞ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ።
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው ባለፉት ሶስት አመታት ከ1300 በላይ አረጋውያንን በበግ ማደለብ፣ በዶሮ እርባታና በጓሮ አትክልት የገቢ ማስገተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዛሬውም ዕለት በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተማ ስርጭቱ የሚቀጥል 327 አረጋውያንን በገቢ ማስገኛ እንዲሰማሩ የዶሮ፣ የመኖና የኬጅ ድጋፍ መርሃ-ግብር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስጀምሯል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አረጋውያን የከተማችን የክብር አንባሳደሮች እና ለትውልዱ የታሪክ ድልድዬች በመሆናቸው ከክብር በተጨማሪ በከተማችን የልማት ጉዞ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ ቢሮው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው፤
መንግስት ልማቶች በተለይም የኮሪደር ልማቱ ለአረጋውያን ተስማሚና ምቹ የማድረግ ስራ መስራቱን በተያያዘም አረጋውያን በልማቱ የእኩል እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በገቢ ማስገኛ በመደገፍ ጊዜያቸውን ከድካም ወጥተው ንቁና ውጤታማ ስራዎችን እንዲሰሩ ያለመ የድጋፍ መርሃ- ግብር መሆኑን ገልፀው ተጠቃሚ አረጋውያንም ባገኙት ድጋፍ በመጠቀም ለአካባቢያቸው ምሳሌ እንዲሆኑ አደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሰራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ቢሮው የተጣለበትን ኃላፊነት በከፍተኛ ተነሳሽነት በመፈፀም የመንግስት የሰው ተኮር ልማቶችን እውን ለማማድረግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተው
በትውልዱ ላይ ለሚጠበቁ ለውጦች ከማሕፀን ጀምሮ እስከ አረጋውያን ከፍተኛ አፈፃፀም ማስመዝገቡን በመግለፅ ለክፍለ ከተማቸው አረጋውያን የተደረገው ድጋፍ የዚህ ማሳያ መሆኑን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ አረጋውያን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ክፍሌ ማሕበሩን ወክለው ባስተላለፉት መልዕክት አረጋውያን መስራት አይችሉም የሚለው አስተሳሰብ በለውጡ መንግስት መሰበሩን አሁን ላይ ከክብርት ከንቲባ ጀምሮ የቢሮው አመራሮች በየደረጃቸው ሰው ተኮር ሰራ ለአረጋውያን ተደራሽ ማድረጋቸው በዚህም ማሕበራቸው እውቅና እደሚሰጥ በቀጣይም ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሕሊና ሐይሌ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማሕበራዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አረጋውያን እድሉ ከተመቻቸላቸው መስራት ይችላሉ በሚል ዓላማ ለክ/ከተማው አረጋውያን ለተደረገው ድጋፍ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ አረጋውያን የዶሮ፣ የመኖና የኬጅ ድጋፎች ከክብር እንግዶች በተቀበሉበት ወቅት ለተደረገላቸው ድጋፍ የደስታ ምስጋናቸው አቅርበው በቀጣይ ራሳቸውንችለው ለመስራት ጥሩ መነቃቃት እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments