በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት እና ፈተናዎች ዙሪያ ምክክር ተካሄደ። መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት እና ፈተናዎች ዙሪያ ምክክር ተካሄደ።
መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው በዛሬው ዕለት በሕፃናት መብት ደሕንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬቱ አማካኝነት በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሕፃናት ሁለንተናዊ እድገት ፈተናዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፣ ከፍትሕ አካላት ፣ ከፓሊስ አባላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ከተማችን ልጆችን ለማሳደግ ምርጧ እና ተምሳሌታዊ ከተማ መሆኗን ለማረጋገጥ መጠነ ሰፊ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው
ይሄንኑ ውጤታማነት ለማስቀጠልም በሁሉም ቦታ ያሉ ሕፃናት መብታቸው ተጠብቆ እና ሁለንተናዊ እድገታቸው ተረጋግጦ ማደግ የሚገባቸው በመሆኑ በማረሚያ ቤትም ከእናቶቻቸው ጋር ያለጥፋታቸው ለሚቀጡ ሕፃናትም በልዩ ትኩረት ልንከውናቸው ስለሚገቡ መብት እና ውክልናቸውን የሚስጠብቁ ተግባራት ለመምከር እና መፍትሄ ለመጠቆም ያለመ መድረክ መሆኑን አብራርተዋል።
በቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በበኩላቸው ቢሮው ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ሕፃናቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት እና ከማረሚያ ቤቱም ጋር በቅንጅት ለመስራት እና አማራጭ የክብካቤ አገልግሎቶች አሠራር ላይ ለመምከር እና የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በዕለቱ የመወያያ ሰነድ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ሕፃናት የሚደርስባቸውን የስነ- ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጫና እና አሳሳቢነት እንዲሁም በእዚሁ ሀሳብ ዙሪያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያጠናው ጥናት በሰነድ የቀረቡ ሲሆን የድጋፍ ክብካቤ ፕሮግራሞች፣ በአሠራር ዙሪያ ባሉ ተግዳሮቶች፣ የባለድርሻ አካላ ሚና እና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የቢሮው የሕፃናት መብት ደሕንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዱዓለም ታፈሰ ዕለቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች በመረጃ የተደገፉ ግልጽና ቀልጣፋ አሰራሮች ለመተግበር የፀጥታ፣ ፍትሕ አካለትና ቢሮው ተቀናጅቶ መስራት ማስፈለጉ እና የተናበበና ወጥ የሆኑ አሰራሮችን በጋራ በመተግበር
በተለይም በውይይቱ ለተነሱ ሃሳቦችን በሰጡት ማብራሪያ ተናቦ ከመስራት ጋር የተነሱት ተገቢነት ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ መድረኩም ያስፈለገው ለዚሁ በመሆኑ በቀጣይም ተከታታይ መድረኮች እንደሚካሄዱ፣ ከህግ ማሻሻያ አንፃር ተሳትፎ እንደሚደረግም አስረድተዋል።
በውይይት መድረኩም የሐይማኖት አባቶች፣ የእድር ምክር ቤት ተወካዮች እንዲሁም የስራው ባለቤት የሆኑ ባለድርሻ አካላት ፣ ከፍ/ቤቶች የዳኞችና የማሕበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች፣ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ሕፃናት ወንጀል መርማሪ አመራሮች፣ ከሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ተወካዬች የተገኙ ሲሆን
በምከክር መድረኩ ከሕፃናት አንፃር ያሉ ተግዳሮቶች፣ ከቅንጅት አሰራር፣ ከጋራ መመሪያ አንፃር የታዩ ክፍቶችን በተለይም የፖሊሲ እና የህግ ማሻሺያ አማራጮች እና አማራጭ እንክብካቤን ለመተግበር የሚያስችሉ የቅርብ እና የረጅም ጊዜ የተግባር እቅድ በማዘጋጀት የጋራ ኃላፊነትን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments