ቢሮው  የፆታዊ ጥቃት ጥቆማዎችን በ#990  ነፃ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው  የፆታዊ ጥቃት ጥቆማዎችን በ#990  ነፃ የጥሪ መቀበያ መስመር ለፖሊስ  እንዲጠቁሙ ጥሪውን ያስተላልፋል። ሚያዚያ  17ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢ

ቢሮው  የፆታዊ ጥቃት ጥቆማዎችን በ#990  ነፃ የጥሪ መቀበያ መስመር ለፖሊስ  እንዲጠቁሙ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ሚያዚያ  17ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

ቢሮው  በሴቶችና ሕፃናት  ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመተባበር  መጠነ ሰፊ ስራዎችን ይከውናል። ከቅድመ መከላከል ግንዛቤ ፈጠራ አንስቶ እስከ ምርመራ እና የፍርድ ሂደትን ጨምሮ ለሴቶች እና ሕፃናት ትኩረት በመስጠት እና በልዩነት ጉዳዩን የሚይዙ ባለሙያዎች በሟሟላት ጭምር ይሰራል።

ከ11ዱም  ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ  በሴቶችና ሕፃናት  ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በተመለከተ በቅርበት የሚሰሩ የፖሊስ አባላት ፣ የጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የወረዳ ባለሙያዎች በተገኙበት አዲሱን የፖሊስ ጥቆማ መስጫ #990 ነፃ የስልክ ጥሪ ትውውቅ የተደረገ ሲሆን 

በተያያዘም የፆታዊ ጥቃት፣ እንዲሁም የፆታዊ ጥቃትን አስመልክቶ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የቅድመ ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ምክክር ተካሂዷል።

በቀጣይም ለህብረተሰቡ  በ #990 ጥቆማ  መስጠት እንደሚችል ለማስገንዘብ በስፋት ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑም ተገልፆል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments