ቢሮው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ፣ የአካል ጉ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ፣ የአካል ጉዳት እና የጤናና የኢኮኖሚያዊ ችግር ለገጠማቸው ሴቶች 52.5 ሚሊየን የሚያወጣ ጉልበት፣ ጊዜ ቆጣቢና የሥራ ጫና የሚቀንሱ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ መርሃ-ግብር አካሄደ። የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ ቢሮ

ቢሮው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ፣ የአካል ጉዳት እና የጤናና የኢኮኖሚያዊ ችግር ለገጠማቸው ሴቶች 52.5 ሚሊየን የሚያወጣ ጉልበት፣ ጊዜ ቆጣቢና የሥራ ጫና የሚቀንሱ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ መርሃ-ግብር አካሄደ።

የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ ቢሮ  

የአዲስ አበበ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት አመት በ11ዱም ክፍለ ከተማ በ119ኙም  ወረዳዎች ለተመለመሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ፣ የአካል ጉዳት እና ጤናና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለገጠማቸው 2102 ሴቶች ጉልበት፣ ጊዜ ቆጣቢና የሥራ ጫና የሚቀንሱ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች የድጋፍ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ  ወቅቱ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 የሚከበርበት ሴቶች ከጓዳ ወደ አደባባይ የወጡበት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሆኑበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው  ዛሬም ሴቶችን ለመደገፍ ቢሮው 52.5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በአስቸጋሪ ጤና ችግር ውስጥ የሚገኙ እና በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ ሴቶች የተዳከመ ተስፋቸውን ለማለምለም በተለየና ዘላቂ በሆነ መንገድ በመደገፍ ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ፣ 

እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ እንዲያቀርቡና መስራትና እንደሚችሉ የሚያስመሰክሩበት እና በቀጣይ በጥረት ወደ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርሱ በማመን የሚደረግ ድጋፍ መሆኑን በመግለፅ የሴቶች ጥንካሬ ለከተማችን ብልፅግና መሰረት መሆኑን ገልፀዋል።

በየቢሮው የሴቶች ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ በበኩላቸው ለተጠቃሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት  እንደገለፁት ሴቶች የሚደርሱባቸውን ጫና ከግምት በመክተት ቢሮው ፕሮጀክት በመንደፍ ጉልበት፣ ጊዜ ቆጣቢና የሥራ ጫና የሚቀንሱ ተስማሚ ቴክኖሎጂ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ግልፅ መስፈርት በማዘጋጀት የተመለመሉ እና  ድጋፉ የተደረገ መሆኑን በአንድ ጊዜ መለወጥ ባይቻልም በጥረት ጠንክሮ በመሥራት ከራስ ባለፈ ለሌሎች አቅም መሆን እንደሚቻል አስረድተዋል። 

አክለውም ወቅቱ ልዩ የሚያደርገው የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን የሚከበርበት ብሎም የምርጫ ዘመን ላይ የምንገኝበት በመሆኑ ሴቶች ንቁ ተሳታፊና ለሀገር እድገት ወሳኝ የሆነ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በመግለፅ ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ እንደ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ፣ ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት፣ የተለያዩ የሴት አደረጃጀቶች፣ ባንኮችና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ለነበራቸው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል። 

በመድረኩ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ማብቃትና ተጠቃሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት  ወ/ሮ ስፍራሽ አልማው የፕሮግራሙን አላማ፣ የተከናወኑ ተግባራትንና የተገኙ ተጨባጭ ስኬቶችን ለተሳታፊዎች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን 
  
በመርሃ ግብሩ ላይ ከአሁን በፊት ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶች በመገኘት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል እዚህ እንዲደርሱ የቢሮው የግብዓትና የሞራል ድጋፍ ወሳኝ እንደነበር ነገር ግን የራስ ጥረት ለሚመዘገብ ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ የበጀት አመቱ አዲስ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን  አበረታተዋል። 

በመጨረሻም ለተመለመሉ እና በምርጫቸው መሰረት በግልና በማሕበር ለተደራጁ  2102 የሚሆኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በመድረኩ በተገኙ ኃላፊዎች የልብስ ስፌት፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች  የእንጀራና ዳቦ ምጣድ፣ የቺፕስ መጥበሻ ማሽን ስርጭቱ በይፋ የተጀመረ ሲሆን 

የእድሉ ተጠቃሚ ሴቶችም ደስታቸውን በመግለፅ ድጋፉን ላበረከተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን በማመስገን በቀጣይም ድጋፉን በውጤት ለመቀየር ጠንክረው እንደሚሰሩም ገልፀዋ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments