50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለዕኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዬጵያ!" በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ። የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለዕኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዬጵያ!" በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።
የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተሴቶች፣ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዛሬው ዕለት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ “GIVE TO GAIN” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ የሚከበር መሆኑን ገልፀው እነዚህ አመታት ሴቶች ከቤት ወደ አደባባይ ተሳትፏቸውን ያረጋገጡበት፣ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸው የተረጋገጠበት ወቅት ላይ መደረሱን በዋነኝነት ሴቶች በሁሉም እርከኖች ውሳኔ ሰጪነታቸው እያደገ የመጣበት ሂደት መፈጠሩን አብራርተዋል።
በዓሉን ስናከብር የሴቶችን ተሳታፊነት፣ ተጠቃሚነት እና እሴቶቻችንን በሚያጎሉ ዝግጅቶች እንደሚከበር በአጠቃላይ በሁሉም መስክ ሚናቸው ጎልቶ እንዲታይ የተደረገበት ሴቶችም እስከ ከተማችን ከንቲባነትና የሀገሪቱ ርዕሰ-ብሔር ደረጃ በመድረስ ብቀታቸውን ያሳዩበት መሆኑን ገልፀው ፆታዊ ጥቃትን ከመከላከል አንፃር የሚቀሩ ነገሮች መኖራቸውን ቢሮው የከተማዋን ሴቶች በማስተባበር በቀጣይም ጥረቶችን እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
የቢሮው የሴቶች ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደገለፁት በቀጣይ በዕቅድ ተይዘው የሚተገበሩ ተግባራትን ይፋ አድርገዋል።
ከብሎክ እና ወረዳ ጀምሮ እስከ ከተማ አቀፍ በሚኖሩ ንቅናቄዎች ከ2ሺህ በላይ ሴት የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሩጫ/እግር ጉዞ፣ 20ሺ ለሚደርሱ ሴቶች የማሕፀንና የጡት ጫፍ ካንሰር ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ 300 በላይ ሴቶችን የሚያሳትፍ ፓናል ውይይት፣ ከ500 በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት የኪነ-ጥበብ ምሽት፣ የእግር ኳስ ውድድር፣ ከ500 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ ተደራሽ ማድረግ፣ የሴት ልማት ሕብረቶችን በመደገፍ ሞዴል ማድረግ፣ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያግዙ ባዛሮችን ከወረዳ እሰከ ከተማ ማዘጋጀት እና የሴቶችን የመራጭ ተመራጭነትና ታዛቢነትን ሚናቸውን የሚያጎሉ ንቅናቄዎች እንደሚደረጉ አጠቃላይ የሴቶችን ተሳትፎ፣ ትብብርንና አብሮነትን የሚያጎሉ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚካሄዱ ለጋዜጠኞች አብራርተዋል።
በዕለቱ ከተገኙ ጋዜጠኞችም ከሴቶች ፆታዊ ጥቃት፣ ከአስተማሪ የሕግ አተገባበር አንፃር እና ከውሳኔ ሰጪነት አንፃር ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments