አዲስ አበባን ሕፃናት ለማሳደግ ምቹ ከተማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋማዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ። የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
አዲስ አበባን ሕፃናት ለማሳደግ ምቹ ከተማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋማዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
አዲስ አበባን ሕፃናት ለማሳደግ ምቹና ምርጥ ከተማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋማዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም መረጃ ማሰባሰቢያ (Kobo) እና በሕፃናት ዘመናዊ ጉዳይ አያያዝ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ስልጠና መድረክ ላይ ተገለፀ።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማች ን አዲስ አበባ ሕፃናት ለማሳደግ ምቹና ምርጥ ከተማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋማዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ለዚህ መሳካት በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ቀጣይና ተከታታይ እድገት አምጪ አሰራሮች መተግበር ወቅቱ የሚፈልገው ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
ቢሮው ወቅቱን የሚመጥኑ አሰራሮችን ከሚተገብርባቸው መካከል በሆኑት በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም መረጃ ማሰባሰቢያ (kobo) እና በሕፃናት ዘመናዊ ጉዳይ አያያዝ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ለመተግበር በማለም የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በስራ ላይ በአግባቡ እንዲተገበር በመድረኩ ለተገኙ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።
የቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በበኩላቸው መተግበሪያዎቹ ስራ ላይ የዋሉ ቢሆንም በተደረገ ክትትል ከሚጠበቅባቸው ፍጥነትና ጥራት አንፃር የሚቀሩ ነገሮች በመታየቱ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ትኩረት እንዲሰጠው በማሰብ እና ወጥ የጋራ አተገባበርን ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን በመግለፅ በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አክለውም መተግበሪያዎቹን በስራ ላይ ለማዋል ለባለሙያዎች አስፈላጊው ስልጠናና ግብዓት መሟላቱን ክፍተቶችን ለመፍታት በቀጣይም ቢሮው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ከተሳታፊዎች ልጆች ላይ የሚሰራው ስራ ትኩረት የሚፈልግ ለነገ ማዘግየት የማይቻል ትልቅ ኃላፊነትን የሚሻ በመሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመተግበር የያዝነውን በፍጥነት የማደግ ጉዞ በጋራ ለማሳካት ርብርብ እናድርግ ሲሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን አያይዘውም ከተግባሩ አፈፃፀም አንፃር ትኩረት የሰጡ አካላት ያስመዘገቡት ውጤት የሚያሳየው አበረታች ለውጥ በመሆኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉም የማበረታቻ ምስጋናቸውን አቅረበው ሌሎችም አበረታች ለውጥ ለማስመዝገብ ጥረት እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የቀዳማይ ልጅነት እድገት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሕይወት ደረሰ በዕለቱ በጉዳዩ ዙሪያ መነሻ ነጥቦችን ከቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አንፃር ዋና ዋና ነጥቦችን አንስተው ባስተላለፉት መልዕክት በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም መረጃ ማሰባሰቢያ (Kobo collector dashboard) መተግበሪ ብዙ የተደከመበትና ኢንቨስት የተደረገበት አዋጭና የታመነበት በመሆኑ ተግባር ላይ በማዋል በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ በመድረኩ የተገኙ ኃላፊዎች በመጪው ትውልድ ላይ የሚሰራውን የከተማ አስተዳደሩ ኢኒሼቲቮችን ለማሳካት ኃላፊነታችንን በጋራ እንወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሕፃናት መብት ደሕንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ታፈሰ በመድረኩ እንደገለፁት የመተግበሪያዎቹ ስኬት የሚለካው በምንሰጠው ትኩረት ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ ልንደርስላቸው የሚገቡ ሕፃናት በእኛ መዘግየት ምክንያት የሚደርስባቸው ጫና ሊቀለበስ የማይችል መሆኑን ተረድተን ለቀጣዩ ትውልድ ዛሬ እንስራ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዕለቱ ከሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማሐበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሕፃናት ዘርፍ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆን ከቴክኖሎጂው አዲስነት አንፃር በቀጣይም ተጨማሪ የተግባር ስልጠናዎች ቢሰጡና ከሰው ኃይል ፍልሰት አንፃር የተመደቡት ባለሙያዎች በመዛወራቸው ሌላ መተካት እድል ቢሰጠን የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ቢሮው ግን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሰፊ ክትትል በማድረግ ለማሳካት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የለሙትን መተግበሪያዎች ባገኙት ግንዛቤ ልክ ለመተግበር እንደሚተጉም ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments