ቢሮው በ2018 በጀት አመት በልብስ ስፌት እና በቆዳ ስራ የሙያ ስልጠናቸውን ለአጠናቀቁ አካል ጉዳተኞች የመስሪያ ግብአት ድጋፍ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አካሄደ። የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
ቢሮው በ2018 በጀት አመት በልብስ ስፌት እና በቆዳ ስራ የሙያ ስልጠናቸውን ለአጠናቀቁ አካል ጉዳተኞች የመስሪያ ግብአት ድጋፍ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አካሄደ።
የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአ/አ/ሴ/ሕ/ማ/ጉ ቢሮ
ቢሮው በ2018 በጀት አመት በልብስ ስፌት እና በቆዳ ስራ የሙያ ስልጠናቸውን ለአጠናቀቁ አካል ጉዳተኞች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ይረዳ ዘንድ በዛሬው ዕለት የቢሮው የበላይ ኃላፊዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የበጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ግዲ በክብር እንግድነት በተገኙበት የመስሪያ ግብአት ድጋፍ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የድጋፉ አላማ በአመለካከት ደረጃ አካል ጉዳተኞች መስራት ይችላሉ የሚለውን በሕብረተሰቡ ውስጥ ለማስረፅ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማስጠበቅ እና በስነ-ልቦና አካል ጉዳተኝነታችሁ ሳይገድባችሁ ሰርታችሁ ስኬት ላይ መድረስ እንደምትችሉ የምናሳይበት ነው ሲሉ ገልፀዋል። አክለውም ዋናው ነገር በተገኘው ድጋፍ ልክ ስኬታማ ለመሆን ጠንክረው እንዲሰሩና አርዓያነታቸውን በተግባር እንዲያረጋግጡ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በቢሮው የማሕበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ ቢሮው በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በተለይም የአካል ጉዳተኞችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ ቢሮው በጀት በመያዝ ድጋፉን በየጊዜው አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን
በያዝነው አመት ለ186 አካል ጉዳተኞች የልብስና የቆዳ ስፌት ማሽኖች ድጋፍ መደረጉን፤ እስካሁን 900 አካል ጉዳተኞች ተደራሽ መደረጉና አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን አስገንዝበዋል። ድጋፉ ከማግኘት በላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባችሁ መሆኑን ተረድተው ጠንክረው በመስራት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል። ለፕሮግራሙ መሳካት የአዲስ አበባ ፉይናንስ ቢሮ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በቢሮው የአካል ጎዳተኞች፣ አረጋውያንና ቤተሰብ ማስተባበሪያ መከታተያ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሕይወት በቀለ በበኩላቸው በመድረኩ ላይ ቢሮው በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ያደረገላቸው አካላት ያስመዘገቡት ውጤት በድምፅና በምስል አስደግፈው አቅርበው በድጋፍ አማካኝነት አበረታች ለውጦች በመመዝገባቸው ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው ያሉበት ድረስ በመውረድ በየጊዜው ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በመድረኩ ላይ ከአሁን በፊት በቢሮው ድጋፍ የተደረገላቸው አካል ጉዳተኞች ያስመዘገቡትን ለውጥ አስመልክቶ ተሞክሯቸውን አቅርበዋል። በዚህም በወረዳና በክ/ከተማ ደረጃ በመስፈርት ተለይተው የስነ ልቦና እና ሌሎች ድጋፎች እንደተደረገላቸው፤ በልዩ ሁኔታ ግን ቢሮው የአቅም ግንባታ፣ የሙያ ስልጠና እና የመስሪያ ግብአት በማግኘታቸው ከራሳቸውና ከቤተሰባቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድል እንደፈጠሩ ይሄ እንዲሳካ ቢሮው ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የበጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ግዲ፣ የአካል ጉዳተኞች ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ይታጠቁ ደርሰህ ፣ የቢሮው ፕሮሰስ ካውንስል አባላት በተገኙበት በ11 ክ/ከተማ በመስፈርት ተለይተው ስልጠናውን ላጠናቁ አካል ጉዳተኞች ለስራ የሚያገለግሉ የልብስና የቆዳ መስፊያ ማሽኖች የግብአት ድጋፍ በቢሮ ኃላፊዎች አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments