ቢሮው የማሕበራዊ ችግር ተጎጂ ለሆኑ የሱዳን ተመ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው የማሕበራዊ ችግር ተጎጂ ለሆኑ የሱዳን ተመላሾች ስልጠና በመስጠት የማቋቋሚያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ። የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

ቢሮው የማሕበራዊ ችግር ተጎጂ ለሆኑ የሱዳን ተመላሾች ስልጠና በመስጠት የማቋቋሚያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው ስልጣን መሰረት  ሰው ተኮር ስራዎቹን  በተሻላ ለህብረተሰቡ ለማድረስ  በተለይም  ለተለያዩ  ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት( ውጤታማነት)  ለማሸጋገር የሚረዱ የተለያዩ መንገዶችን በመፈተሽ በየጊዜው ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አካሄዶችን ይቀይሳል።

በዛሬውም ዕለት ከቀድሞ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከአስረአንዱም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ በሱዳን በተፈጠረ ግጭት ወደ ሀገራቸው የተመለሱ  የማሕበራዊ ችግር ተጎጂ ለሆኑ የሱዳን ስደት ተመላሽ ኢትዬጵያውያን የልል ስልጠና /soft skill/  ስልጠና በመስጠት እና በማብቃት እንደየምርጫቸው በገቢ ማስገኛ የሚሰማራቸውን የማቋቋሚያ ቁሳቁስ ድጋፍ መርሃ-ግብር አካሂዷል።  

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ  በዕለቱ በአስተላለፉት መልዕክት መሰል ድጋፎች መንግስት ለስደት ተመላሾች የሰጠውን ትኩረት ማሳያ በመሆኑ የተገኙ ድጋፎችን በውጤት እንዲቀይሩ አደራ ብለዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር  ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው ድጋፉ ለሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መድረሱን በማረጋገጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ድጋፉን ላስተባበረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ  ምስጋና አቅርበዋል።

የቢሮው የማሕበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው  እንደገለፁት በሱዳን በተፈጠረ ግጭት የስደት ተመላሾቹ የገጠማቸውን ችግር ቢሮው በመከታተል መገንዘቡን እንዲሁም ለድጋፉ ብቁ ለማድረግ  ብዙ ክትትሎችን በማድረግና ስለጠናዎችን በመስጠት ለዛሬው የቁሳቁስ ድጋፍ ቀን መደረሱን ገልፀው በቀጣይም ውጤታማ እንድትሆኑ ድጋፎች እና ክትትሎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበው ከገጠማችሁ ችግር ለመውጣት ጥረቶች ማድረግ ከተጠቃሚዎች እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።  

በዕለቱ የድጋፍ ተጠቃሚዎቹ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ግጭቱ የተከሰተበት ወቅት ድንገተኛ መሆኑንና በሱዳን ያፈሩትን ንብረት ጥለው መውጣታቸውን ወደ ሀገር ሲመለሱ ብዙ ችግሮች እንዳሳለፉ ገልፀው ችግራቸውን በመረዳት ድጋፉን ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዕለቱ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ የሱዳን ተመላሽ ስደተኞች ከስልጠና በኃላ በመረጡት መሰረት  የሽንኩርት መፍጫ፣ የቺፕስ ማሽን፣ ፔርሙስ፣ የእንጀራና የዳቦ ምጣዶች ድጋፎች ተደርጎላቸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments