ቢሮው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተስማሚ ችሎት አገልግሎት የሚሆኑ ግምታቸው ከ350,000 ብር በላይ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ። ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተስማሚ ችሎት አገልግሎት የሚሆኑ ግምታቸው ከ350,000 ብር በላይ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
በከተማችን ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ጥቃት የደረሰባቸው ሕፃናት፣
ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ምስክርነታቸውን በነፃነት በመስጠት ፍትህ ማግኘት እንዲችሉ ለዚህ አገልግሎት የሚውል የተስማሚ ችሎት
አገልግሎት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ይከናወናል።
ቢሮው ይህ ተስማሚ ችሎት ፍትህ "ሰው ተኮር" እንዲሆን የሚያደርግ ድልድይ መሆኑን በማመን በዛሬው ዕለት የተስማሚ ችሎት ማዕከላትን ለማደራጀት የሚውሉ ግምታቸው ከ350,000 ብር በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮችን ፣የሕፃናት መጫዎቻዎችን፣ የስዕል መሳያ ደብተሮችን ፣ማርከሮችን ፣ የሕፃናት ወንበሮችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በማሰባሰብ አበርክቷል።
በዕለቱ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር አህመድ፣ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ፣ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የቢሮው የማህበራዊ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው የተገኙ ሲሆን
ተስማሚ ችሎት አገልግሎት ጽንሰ-ሀሳብ በኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው በፍትህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች (በተለይም ህፃናት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች) ያለምንም ፍርሃት፣ ጭንቀት እና ጫና እውነታውን እንዲናገሩ ታስቦ የተዘጋጀ ልዩ የችሎት አካባቢ በመሆኑ ለፍትህ ሥርዓቱ ጥራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት
በተለይም ሥነ-ልቦናዊ ደህንነት፣ እውነተኛ መረጃ ለማግኘት፦ ህፃናት ወይም ተጋላጭ ወገኖች ፍርሃት በሌለበት አካባቢ እውነቱን በነፃነት እንዲናገሩ ስለሚያስችል ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት እንዲሁም ሰብአዊ መብትን ማክበር፦ የጥቃቱ ሰለባዎች በፍትህ ሂደት ውስጥ በድጋሚ ሌላ ስቃይ (Secondary Victimization) እንዳይደርስባቸው ለመከላከል ጠቃሚ መሆኑን
በተጨማሪም የችሎቱ ተጠቃሚዎች የከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን እና በቤተሰብ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና የድጋፍ ስራዎችን አስመልክቶ በቀጣይም የጋራ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ መክረዋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤትም በድጋፉ መደሰታቸውን በመግለፅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን አመስግነዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments