ቢሮው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግርን  አስ...

image description
- In ሴቶች    0

ቢሮው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግርን  አስመልክቶ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር አከናወነ። ጥር  09 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

ቢሮው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግርን  አስመልክቶ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር አከናወነ።

ጥር  09 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው ስልጣን መሰረት  ሰው ተኮር ስራዎቹን  በተሻላ ለህብረተሰቡ ለማድረስ  በተለይም  ለተለያዩ  ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የሚረዱ የተለያዩ መንገዶችን በመፈተሽ በየጊዜው ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አካሄዶችን ይቀይሳል።

በዛሬውም እለት ከዩኒሴፍ ኢትዮዺያ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለነፍሰጡር እናቶችና ከአንድ አመት በታች ላሉ ሕፃናት የሚደረግ የገንዘብ ድጎማ እና ቀጣይ የፕሮጀክቱ ሽግግርን አስመልክቶ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከሚሆኑ 263 እናቶች እና ሕፃናት በተገኙበት ከክፍለ ከተማው ስራ አስፈፃሚ እና  ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ጋር በመሆን የማብሰሪያ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ  መርሀ-ግብሩን አከናውኗል። 

በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለይ የክብርት ከንቲባችን ኢኒሼቲቭ አዲስ አበባ ሕፃናት ለማሳደግ ምቹና ወደፊት የወጣች ከተማ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን የዕለቱ የድጋፍ መርሀ ግብርም  ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በተለይም ደግሞ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ሕፃናትን ህይወት ለመለወጥ ያለመ አዲስ ምዕራፍ የተጀመረውን ኢኒሼቲቭ ከማጠናከር ባሻገር የቤተሰቦችን ማህበራዊና ኤኮኖሚ ጫና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ  እንዳለው ገልፀዋል።

አክለውም ዩኒሴፍ ን ጨምሮ ፕሮጀክቱን ያመቻቹ እና ተሳትፎ ያደረጉ አካላትን በቢሮው ስም በማመስገን  የዕለቱ  ድጋፍ ከገንዘብ በላይ ፤ በመሆኑ  የእናቶችን  ጥንካሬ የምናከብርበትና ለልጆቻቸው ጤናማ እድገት ያለንን ቁርጠኝነት የምናሳይበት መንገድ ነው በመሆኑ  የቤተሰብ መሰረት የሆናችሁ  እናቶች ፤ እናንተ ስትጠነክሩ ማህበረሰቡ ይጠነክራል፣ ሀገርም ትለማለች እና ድጋፉን  ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግር ለማድረግ እንድትጠቀሙት አደራ እላለሁ ብለዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው  ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መርህ የሚከናወነው ፕሮግራም ለትውልድ ግንባታ ከፍ ያለ  አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ በቀጣይም የማሸጋገር ሂደት ስራዎችን በጋራ መምራት እንደሚገባ ገልፀዋል። 

የዩኒሴፍ በኢትዮዺያ ተወካይ አቶ ሽመልስ ተሰማ ፕሮጀክቱን አስመልክተው ባቀረቡት ሰነድ እንደገለፁት የፕሮጀክቱ ዓላማ ከድጎማ ባሻገር  የአመጋገብ ስርዓትን የማሻሻል  እና በተለያዩ ስልጠናዎች በማብቃት ከራሳቸው አልፈው ወደ ምርታማነት በመሻገር ለሀገር አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማገዝ መሆኑን አብራርተዋል።

 በክፍለ ከተማው የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይታይሽ ደነቀው የድጋፍ ተጠቃሚዎችን ከመለየት ጀምሮ በጥንቃቄ እየተከናወነ የሚገኝ የመንግስትን የተረጂነት ቅነሳ እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚያግዝ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው ለፕሮጀክቱ መሳካትም ፅ/ቤቱ ድጋፍ እና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ፣ የዩኒሴፍ በኢትዮዺያ ተወካይ አቶ ሽመልስ ተሰማ፣ በክፍለ ከተማው የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይታይሽ ደነቀው እንዲሁም  የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን 

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በተፈጠረላቸው እድል በእጅጉ መደሰታቸውን በመግለፅ ውጤታማ አምራች ለመሆን እንደሚሰሩም ገልፀዋል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments