ቢሮው ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን ጋር በጋራ በሴቶችና ሕፃናት ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ዙሪያ በተጠና ጥናት ላይ ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አደረገ።
ቢሮው ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን ጋር በጋራ በሴቶችና ሕፃናት ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ዙሪያ በተጠና ጥናት ላይ ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አደረገ።
ታህሳስ 23 ቀን 2018ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው የሚሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች በተሻለ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሚረዱ የተለያዩ መንገዶችን ለመፈተሽ በየጊዜው ከተለያዩ የጥናት ማዕከላት ጋር በመተባበር ጥናቶችን እና አካሄዶችን ይመረምራል።
በዛሬው ዕለትም የበላይ አመራሮች እንዲሁም ጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር በጋራ በመሆን ጥናቱን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።
የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ እና የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ ጥናት መፍትሄ ጠቋሚ በመሆኑ በተለይም ፆታን መሰረት ያደረጉ በሴቶችና ሕፃናት ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ዙሪያ የሚደረግ ጥናት ለቢሮው የሚኖረው ፋይዳ ከፍ ያለ መሆኑን አውስተው ጥናቱን እንደ ግብዐት ለመጠቀም ቢሮው ዝግጁ መሆኑን በመድረኩ አስረድተዋል።
በእለቱ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከመጡ የጥናት ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ከተማ የጥቃት ሁኔታ፣ የጥቃት መንስኤዎች ፣ ጥቃት ያለው ተፅዕኖ እና ጥቃት በአዲስ አበባ ከተማ ሳቢና ገፊ ምክንያቶችን በሚዳስስ ጥናት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቢሮው የጠቅላላ ካውንስል አባላት በጥናቱ ወሰን ፣ አላማውና የጥናቱ ተሳታፊዎች ዙሪያ ሀሳቦች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በቀጣይም ጥናቶቹን በማሳደግ አውደ ጥናት በማዘጋጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመወያየት ጥናቱን ለማሳደግ እንደታሰበ በመድረኩ ተመላክቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments