አካል ጉደተኞችን የሚያካትት ማሕበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማሕበራዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል መዝጊያ ፕሮግራም ተካሄደ።
አካል ጉደተኞችን የሚያካትት ማሕበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማሕበራዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል መዝጊያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አማካኝነት "አካል ጉደተኞችን የሚያካትት ማሕበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማሕበራዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት የመዝጊያ ስነ-ስርዓቱን በየካ ክ/ከተማ ሰፖርት ማዘውተሪያ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ተወካይና የሴቶች ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ "አካል ጉደተኞችን የሚያካትት ማሕበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማሕበራዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ ለቆየው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል መዝጊያ ፕሮግራም እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልዕክት በአስተላለፉበት ወቅት እንደገለፁት
አካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው እንደሚችሉ የታየበትና እንደሚችሉ ያረጋገጡበት ሰፊ ንቅናቄ መሆኑንና በስፖርታዊ ጨዋነትና መከባበር በንቃት በመሳተፍ ብርቱ ፋክክር የታየበት ሰላማዊ ውድድር ሆኖ የተጠናቀቀ በመሆኑ ሁሉንም ተሳታፊዎች፣ ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው ቢሮው ለአካል ጉዳተኞች መብትና ደሕንነት መጠበቅና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አጥብቆ እንደሚሰራምና ከተማችንን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይና የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ከስፖርታዊ ውድድሩ በርካታ ብቁ ስፖርተኞች መገኘታቸውን ሁሉም ክ/ከተሞች በንቃት የተሳተፉበት ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን እና ቢሯቸው አካል ጉዳተኞችን በሰፖርታዊ ልማት ስራዎች ያካተቱ ስራዎችን እንደሚያጠናክሩ ገልፀው ለተሳተፉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአካል ጉዳተኞችን ማሕበርን ወክለው መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ደሳለኝ እሸቱ ፌስቲቫሉ በሰላምና በማረ መልኩ በመጠናቀቁ ደስታቸውን ገልፀው ውድድሩም እንደምንችል ያሳየንበት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በማሕበራቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአካል ጉዳተኞች ማሕበራት ተወካዮች፣ የየካ ክ/ከተማ አመራሮች፣ የከተማዋ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ማህበር ስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች እና የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት በካሳንቺስ አካባቢ በሚገኘው ስፓርት ማዘውተሪያ ተካሂዷል።
በመጨረሻም በተለያዩ ስፖርት አይነቶች ውጤት ላመጡ አካል ጉዳተኛ ስፖርተኞች በደረጃቸው የዋንጫ ሽልማት ከዕለቱ ከተገኙ አመራሮች ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ፣ ከአቶ ዳዊት ትርፋ እና ከሌሎች የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments