በከተማዋ የሚከናወኑ የልማትፕሮጀክቶች ሲቀረፁ ጀ...

image description
- In ሴቶች    0

በከተማዋ የሚከናወኑ የልማትፕሮጀክቶች ሲቀረፁ ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን በባለቤትነት ማሳተፍ እና ማማከር ጠቀሜታው የጎላ ነው ፡:

በከተማዋ የሚከናወኑ የልማትፕሮጀክቶች ሲቀረፁ ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን በባለቤትነት ማሳተፍ እና ማማከር ጠቀሜታው የጎላ ነው ፡:
                   ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ 
 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

ታህሳስ 14 ቀን 2018ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ  “ በዓለም ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ለ33 ኛ ጊዜ“አካል ጉዳተኞችን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት!” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ሁነቶች ሲያከብር የቆየውን የአካል ጉዳተኞች ቀን ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ መድረኩን አከናወነ። 

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት  የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞችን ቀን  ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በተለያዩ ፕሮግራሞች ሲካሄድ መቆየቱንና በእነዚህም ቀናት የግንዛቤ ማሳደግ  ስራዎች መሰራታቸውን በመግለፅ 

በዓሉ ስለ አካል ጉዳተኝነት ግንዛቤ የሚፈጠርበት ብቻ ሳይሆን የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚጠቅም  ከመሆኑም በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞችን ቀን ማክበር ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝና የአካል ጉዳተኞችን ክህሎት በማዳበር፣ ፓሊሲም ጭምር ለመቅረፅ የሚያስችል ነው ሲሉ የቢሮው ኃላፊ ገልፀዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር አካል ጉዳተኞች በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው እንዲሰሩ ከማድረግ ባለፈ በከተማዋ የሚከናወኑ ማናቸውም የልማትፕሮጀክቶች ሲቀረፁ ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን በባለቤትነት ማሳተፍ እና ማማከር ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

በቢሮው የማህበራዊ  ዘርፍና ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው የአካል ጉዳተኞችን  ጉዳይ አጀንዳ በማድረግና  አጋርነትን በማረጋገጥ የመፍትሄ  ሃሳብ በማስቀመጥ በርካታ እንቅስቃሴዎች ሲካሔድ መቆየቱንና 

በታቀደው ልክ ግቡን መምታቱን ለዚህም ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀሪ ጊዜያትም የድርሻችንን ወስደን እንድንቀሳቀስ በማወቅም ባለማወቅም አካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለመከላከል ወደኋላ ሳንል የምንተጋበት በውጤቱም የአካል ጉዳተኛን መብት በማስጠበቅ የከተማችንን ብልፅግና እናረጋግጥ  ሲሉ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካል ጉዳተኞች ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ይታጠቁ ደርሰህ አካል ጉዳተኞችን ለማብቃት ማህበሩ ከአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር እንደሚሰራ ጠቁመው በዓሉን ስናከብር ሁሉም የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ የራሱ አድርጎ ሊወስደው ይገባል ብለዋል።

በዕለቱ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለውይይቱም መነሻ የሆነ በቢሮው የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ፣ ቤተሰብ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት በቀለ አካል ጉዳተኞችን የተመለከተ እየተከናወኑ ያሉ  ተግባራትን አስመልክቶ ሰነድ አቅርበዋል።

በማጠቃለያ መድረኩ በተለያዩ ሙያ ስልጠና በመውሰድ አምራች የሆኑ አካል ጉዳተኞች ምርቶቻቸውን አስጎብኝተዋል፣ የተለያዩ አይነት የአካል ጉዳተኞች ተሰጥኦቸውን አሳይተዋል፣ አስተማሪ ጭውውት እንዲሁም ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር የሚኖሩ ታዳጊዎችም ምርቶቻቸውን ያስተዋወቁ ሲሆን 

በቢሮው በተመቻቸላቸው ዕድል በመጠቀም በተለያዩ ሙያ ስልጠና በመውሰድ ውጤታማ አምራች የሆኑ አካል ጉዳተኞች የእውቅና መርሀ-ግብርም ተካሂዷል።

በዕለቱ የቢሮው የበላይ አመራሮችን ጨምሮ፣ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከተቋማት፣ ከሲቪል ማህበራት፣ የእድር ም/ቤት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በመድረኩ መደሰታቸውንና ጠቃሚ ቁምነገሮችን መቅሰማቸውን በመግለፅ በቀጣይም አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ እና የጋራ ስምምነት ተፈጥሯል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments