ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!!
ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!!
በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ "ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን ዓለም ዐቀፉን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ቀናትን አስመልክቶ የእግር ጉዞ ተካሄደ።
ኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በሀገራችን ደሞ ለ20ኛ ጊዜ "ጥቃትን የማይታገስ ማሕበረሰብ ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የሚታወሰውን አለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ቀናትን በልዩ ልዩ ሁነቶች በርካታ ክንውኖችን በማከናወን ላይ ይገኛል።
በዛሬውም ዕለት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላን ጨምሮ የቢሮውና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የፍትህ አካላት፣ የትምህርት ቤት አካላት፣ የእድር ም/ቤት ተወካዮች ፣ የተለያዩ የሴት ማህበራት እና አደረጃጀቶች አመራር እና አባላት እንዲሁም ከ11ዱም ክ/ከተማ የተውጣጡ ሴቶች በተገኙበት ከሴቶች አደባባይ እስከ አራት ኪሎ አደባባይ የእግር ጉዞ አካሂዷል።
በዕለቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ቢሮው የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ቀናትን ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮቹ በልዩ ልዩ ህብረተሰቡን ባሳተፉ ሁነቶች ሲያከብር እንደቆየ ጠቅሰው
የዕለቱ የእግር ጉዞም በማንኛውም ሁኔታ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ወሲባዊ ጥቃቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሀገራችን ፈርማ የተቀበለችውን ስምምነት የሚፃረር ተግባር በመሆኑ ድርጊቱን ማውገዝና አምርረን መታገል ይኖርብናል የሚለውን መልዕክት በአፅኖት ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
አያይዘውም ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትን በተለይም የአዲስ አበባ ፖሊስ የፀጥታ አካላትንና የማርሽ ባንድ አባላትን በቢሮው ስም አመስግነዋል።
በእግር ጉዞ ላይ ሴት እናት፣ እህት፣ ሚስት እና ሴት ለሀገር ግንባታ አይነተኛ ሚና የምትጫወት መሆኗን በመግለፅ የሴቶች ጥቃት እንዲቆም፣ መብታቸው እንዲከበር እና የፍትህ አካላትም ጥቃት አድራሾችን በማውገዝና አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድ ተሳታፊዎች ድምፃቸውን አሰምተዋል።
የእግር ጉዞውን የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የቢሮው የሴቶች ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይመኙሻል፣ የሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ እናታለም፣ የቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ የመሩት ሲሆን የከተማ አመራሩ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አካላት፣ የሁሉም ክ/ከተማ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና የተለያዩ የሴት ማሕበራት አመራሮችና ተወካዬች ተገኝተው ድምፃቸውን አሰምተዋል።
የተለያዩ የሐይማኖት አባቶች እና የሕዝብ አደረጃጀት ወንድ አመራሮች በእግር ጉዞው ላይ በመገኘት አጋርነታቸውን ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments