
ቢሮው የበጀት ዓመቱ የዘጠና ቀናት እቅድ አፈፃፀም ሂደትን ጨምሮ በሌሎች በርካታ አጀንዳዎች ላይ ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።
ቢሮው የበጀት ዓመቱ የዘጠና ቀናት እቅድ አፈፃፀም ሂደትን ጨምሮ በሌሎች በርካታ አጀንዳዎች ላይ ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።
ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ
ቢሮው ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስችል የ2017 በጀት ዓመት የልማት ዕቅድ እና ለዚሁ እቅድ መሳካት መሳሪያ የሆኑትን የመልካም አስተዳደር እና የሌብነትና ብልሹ አሰራር ማክሰሚያ እቅድ፣ የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው የክ/ከተሞችና የማዕከል አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግና ግብዓት በመውሰድና በማካተት ወደ ትግበራ ገብቷል።
ከእዚህም በተጨማሪ ቢሮው በበጀት አመቱ ከማዕከል ጀምሮ በስሩ በሚገኙ 6ቱም ተቋማት ተፈፃሚነት ያለው የዘጠና ቀናት እቅድን አቅዶ ግብ ተኮር እንቅስቃሴዎችን በመከፋፈል ሲከውን የቆየውን የተግባራት ሂደት አፈፃፀሙን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል።
በቢሮው ስር የሚገኙ ተቋማት ኃላፊዎች የበጀት አመቱ የዘጠና ቀናት የእቅድ አፈፃፀም ሂደት በተለይም ተቋምን ከመለወጥ እና ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር ፣ በፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ሂደት እንዲሁም የሌማት ቱሩፋት እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በእለቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የዘጠና ቀናት እቅዱ አፈፃፀምን አስመልክቶ የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናውን ገልፀው በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት
የቢሮው ማህበረሰብ በአንድነት የችግኝ ተከላ መረሀ ግብሩን እንደሚከውን እና የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት እንዲሁም የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ለማስቀጠል ሊሰሩ የሚገባቸው ክንውኖች ተጠናክረው በመቀጠል በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንደአለባቸው አሳስበዋል።
የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሰመድ ሻሚል በበኩላቸው ቢሮው ታች ድረስ ባለው መዋቅሩ የጀመራቸውን የ90 ቀናት ስራዎች አፈፃፀም በየጊዜው በመገምገም እና የጋራ በማድረግ እንዲሁም በመቀናጀት የያዝናቸውን ግቦች ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ሊያበረክት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
ከእዚህም በተጨማሪ በእለቱ የቢሮው የመካከለኛ ዘመን እቅድ አፈፃፀም ሰነድ በቢሮው የእቅድ እና በጀት ዝግጅት ድጋፍ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አቶ አጥላው ተ/ፃዲቅ አማካኝነት ሰነድ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ዙሪያም የጠቅላላ ካውንስል አባላት የተጀመሩ አካሄዶችን ፈትሾ ለማስተካከል የሚረዳ ሰፊ ውይይት አድርገውበታል።
በዕለቱ በቢሮው ሊቋቋም ስለታሰበው የመማከርት ጉባኤ ዙሪያም ውይይት የተካሄደ ሲሆን የተጀመሩ ስራዎችን በጊዜው ለማከናወንም የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ወደ ስራ ለማስገባት በመስማማት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments