
በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በቢሮው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎች ምልከታውን አጠናቀቀ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በቢሮው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎች ምልከታውን አጠናቀቀ፡፡
ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡዱን የቢሮውን የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ላይ ያከሄደው የሰነድና የአካል ምልከታ አጠቋል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡዱኑ ከቢሮው እቅዶች እና ሪፖርቶች በመነሳት ያደረገው ምልከታ በቢሮው አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ማዕከላት በክበበፀሐይ የሕፃናት ጊዜያዊ ማቆያና ክብካቤ እና የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ልማት ማዕከላት የአካል ምልከታ አካቷል፡፡
ቡዱኑ በሰነድ እና በአካል ምልከታው ግኝት ረቂቅ ሪፖርት ለቢሮው አመራሮችና የጠቅላላ ካውንስል አባላት አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በግኝት ሪፖርት ውይይቱ ቢሮው በመንግስት ስራዎች ያከናወናቸው ተግባራት የተሻለና የተሰጠውን ተልእኮ በተገቢው እየተወጣ መሆኑን የሱፐርቪዥን ቡዱኑ ማረጋገጡ ቡዱኑን የመሩት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ገልዋል፡፡
ወ/ሮ ፀሐይ አያይዘውም ቢሮው በመንግስት ስራዎች እያከናወናቸው ባለው ልክ የፓርቲ ስራዎች ላይ በአንዳንድ የህብረትና የቤተሰብ አደረጃጀቶች ላይ የታዩት መረጃ አያያዝ ክፍተቶች ሊታረሙ ይገባል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments