የቢሮው አመራር እና የጠቅላላ ካውንስል አባላት...

image description
- In ሴቶች    0

የቢሮው አመራር እና የጠቅላላ ካውንስል አባላት የተቋማትን ምቹነት ለማሳደግ በሚረዱ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

የቢሮው አመራር እና የጠቅላላ ካውንስል አባላት የተቋማትን ምቹነት ለማሳደግ በሚረዱ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

ቢሮው ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስችል የ2017 በጀት ዓመት የልማት ዕቅድ እና ለዚሁ እቅድ መሳካት መሳሪያ የሆኑትን የመልካም አስተዳደር እና የሌብነትና ብልሹ አሰራር ማክሰሚያ እቅድ፣ የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው የክ/ከተሞችና የማዕከል አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግና ግብዓት በመውሰድና በማካተት በበጀት አመቱ ልዩ ልዩ ተግባራትን ሲከውን መቆየቱ ይታወቃል።

ከእዚህም በተጨማሪ ቢሮው በስሩ የሚገኙ 6ቱን ተቋማት ለማገዝ እንዲሁም ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ በተለያዩ ጊዜያት ልዩ ልዩ ክትትሎችን ያደርጋል።

በዛሬው እለት ተቋማት የበጀት አመቱ የእቅድ አፈፃፀም በተለይም ተቋምን ከመለወጥ እና ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር እንዲሁም የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የወሰዱትን እርምጃዎች አስመልክቶ የ 3 ተቋማት ክንውን እና አሁናዊ ሁኔታ የሚገልፅ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን

በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያም የቢሮው አመራር እና የጠቅላላ ካውንስል አባላት የተጀመሩ አካሄዶችን ፈትሾ ለማስተካከል የሚረዳ ሰፊ ውይይት አድርገውበታል።

በውይይቱ ላይ የተገኙ የቢሮው የበላይ አመራሮችም የከተማውን ም/ቤት ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በተደረገ ምልከታ እና ምልከታውን አስመልክቶ የተሰጡ አስተያየቶች ን መነሻ በማድረግ ከመደበኛው ተግባራት ውጪ የተሰሩ ስራዎችን ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር በጥልቀት ከገመገሙ በኃላ

የተጀመሩ መልካም ጅምሮችን ለማስቀጠል ጠቃሚ የሆኑ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments