የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱ...

image description
- In ሴቶች    0

የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱ የዘጠና ቀናት እቅድ እና ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱ የዘጠና ቀናት እቅድ እና ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ. ቢሮ

ቢሮው ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስችል የ2017 በጀት ዓመት የልማት ዕቅድ እና ለዚሁ እቅድ መሳካት መሳሪያ የሆኑትን የመልካም አስተዳደር እና የሌብነትና ብልሹ አሰራር ማክሰሚያ እቅድ፣ የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው የክ/ከተሞችና የማዕከል አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግና ግብዓት በመውሰድና በማካተት ወደ ትግበራ ገብቷል።

ከእዚህም በተጨማሪ በበጀት አመቱ ቀጣይ ዘጠና ቀናት በከተማ ደረጃ ሊከወኑ የታቀዱ ተግባራትን ቢሮው ወደራሱ በመውሰድ ከማዕከል ጀምሮ በስሩ በሚገኙ 6ቱም ተቋማት ተፈፃሚነት ያለው የዘጠና ቀናት እቅድን አቅዶ ግብ ተኮር እንቅስቃሴዎችን በመከፋፈል አፈፃፀሙን በተመለከተ የጠቅላላ ካውንስል አባላት ሰፊ ውይይት አድርገውበታል።

በእለቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የዘጠና ቀናት እቅዱ በርካታ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ግቦችን የሰነቀ መሆኑን ጠቁመው በተለይም ቢሮው በስሩ በሚገኙ ተቋማትም ጭምር በፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ዙሪያ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥልበት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቢሮውን የዘጠና ቀናት እቅድ አስመልክቶ የውይይት ሰነዱን የቢሮው አማካሪ ታደለ ደመኮ (ዶ/ር) ያቀረቡ ሲሆን ቢሮው በቀጣይ ዘጠና ቀናት የያዛቸውን ግቦችን ለማሳካት በመናበብ እና በመቀናጀት ሁሉም የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በቢሮው የማህበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው ቢሮው በመደበኛነት ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን የማስተባበር እና በተለይም በተቋማት ውስጥ የተጀመሩ የከተማ ግብርና ስራዎችን የማላቅ ተግባሩን አጠንክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በተያያዘም በቢሮው ስር በሚገኙ ተቋማት የበጀት አመቱ የእቅድ አፈፃፀም በተለይም ተቋምን ከመለወጥ እና ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር እንዲሁም የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያም የጠቅላላ ካውንስል አባላትም የተጀመሩ አካሄዶችንም ፈትሾ ለማስተካከል የሚረዳ ሰፊ ውይይት አድርገውበታል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments