#የተሻሻለ_የቤተሰብ_ስራና_ገቢ_ለሀገር_ኢኮኖሚ!

image description
- In ሴቶች    0

#የተሻሻለ_የቤተሰብ_ስራና_ገቢ_ለሀገር_ኢኮኖሚ!

#የተሻሻለ_የቤተሰብ_ስራና_ገቢ_ለሀገር_ኢኮኖሚ!

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የአካል ጉዳተኞች እና አረጋዊንን መብት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ የወጡ ሕጎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን አፈጻጸማቸውን የመከታተል፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ እና የአገሪቱ (የመዲናዋ) ዝርዝር የልማት እቅዶች የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን ፍላጎት ያገናዘቡ መሆናቸውን የማረጋገጥና የመሳሰሉት ቀዳሚ ግዴታዎች አሉበት፡፡

በቢሮው የአካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያንና ቤተሰብ ማስተባበሪያ መከታተያ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የቤተሰብ ቀንን የቢሮው የበላይ አመራሮች በተገኙበት ከቢሮው ሰራተኞች ጋር “የተሻሻለ የቤተሰብ ስራና ገቢ ለሀገር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች አክብሯል።

በእለቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የቤተሰብ ቀን ተገቢውን ትኩረት ማግኘት ያለበት እና ለሀገር ግንባታም ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አውስተዋል።

በቢሮው የማህበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው ቢሮው ከሚከውናቸው በርካታ ተግባራት መካከል የቤተሰብ ጉዳዮች መካተታቸው ዘርፉ ጠንካራ እና የተሻለ ትኩረት እንዲኖረው ያደርጋል ብለዋል።

ለቤተሰብ ዋጋ መስጠት ለሀገር ዋጋ መስጠት በመሆኑ የቤተሰብን ስራ እና ገቢ ማሳደግ ቤተሰብም በኢኮኖሚ እጥረት እንዳይበተን ከማድረጉም በላይ የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ ነው ብለዋል።

በእለቱ የቤተሰብ ቀንን አስመልክቶ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ሌሎች አስተማሪ ፕሮግራሞች ቀርበውበታል በቀረቡ ፕሮግራሞችም በርካታ ትምህርቶችን እንደቀሰሙ ተሳታፊ የቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ገልፀዋል።

በተጨማሪ በትዳር ዕድሜ ዘመናቸው ውጤታማ ሴት የቢሮው ሰራተኛ ለአዲስ ተጋቢ ሴት የቢሮው ሰራተኞች ተሞክሮ ሽግግር ተካሂዷል።

በመጨረሻም የአንድ ቤተሰብ ውጤታማነት የሚያስተምር የመድረክ ድራማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ባህል ቡድን ቀርቦ ተጠቃሎል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments