የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እ...

image description
- In የኽጻናት    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የክበበ ፀሀይ የሕፃናት ጊዜያዊ ማቆያ እና እንክብካቤ ማዕከልን ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የክበበ ፀሀይ የሕፃናት ጊዜያዊ ማቆያ እና እንክብካቤ ማዕከልን ጎበኙ።

መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

ቢሮዉ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን በየደረጃው የመዘርጋት፣ የመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ማህበራዊ ችግሮችን በመከላከል የህፃናት፣ የሴቶች፣ የአረጋዊያን እና የአካል ጉዳተኞች መብትና ደህንነት ተጠብቆ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የእኩል እድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በርካታ ስራዎችን ይሰራል።

ከእነዚህ ዘርፈ ብዙ ሰው ተኮር ተግባራቶቹን ከሚከውንባቸው ተቋማት ውስጥ አንዱ በሆነው እና በበጀት ዓመቱ ብቻ ከ330 በላይ ሕፃናትን በተቀበለው የክበበ ፀሀይ የሕፃናት ጊዜያዊ ማቆያ እና እንክብካቤ ማዕከልን በዛሬው እለት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የቢሮው የበላይ አመራሮች በተገኙበት ጎብኝተዋል።

ወ/ሮ ቆንጂት በጉብኝታቸው የተቋሙን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች፣ የሕፃናት አያያዝና እንክብካቤዎችን እንዲሁም የግብዓት አቅርቦትን በቅርበት ለማየት መቻላቸው እና ቢሮው የሚተገብረው የማህበራዊ እክል ተጎጂ የሆኑ ሕፃናትን የመንከባከብ ስራ ሰብአዊነት የተሞላው ተግባር በመሆኑ የእዚህም ምስጉን ስራ አካል መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

አክለውም በቀጣይ በተቋሙ የተጀመሩ ስራዎች የሚቀጥሉበትን መንገድ ከቢሮው የስትራቴጂክ ካውንስል ጋር በጋራ እንደሚመክሩበትም አሳውቀዋል።

በቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በበኩላቸው ቢሮው ተቋሙ ለሕፃናቱ ምቹ እንዲሆን በየጊዜው የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የገለፁ ሲሆን በተለይም ከሕፃናቱ ጤና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ከጤና ቢሮ እና ከህክምና ጣቢያዎች ጋር በቋሚነት በሚሰሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በቴክኖሎጂውም ዘርፍ ከሲቪል ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን በማዕከሉ እየበለፀገ ስለሚገኝ የዘመናዊ መረጃ አያያዝ ሶፍትዌር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ይህንንም የተሟላ ለማድረግ የዳታ ምዝገባ ስራ እየተሰራ መሆኑ እና ወደ ተቋሙ በሚመጡ ሕፃናት መረጃ ዙሪያም ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውንም ገልፀዋል።

በእለቱም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ፣ በቢሮው የሕፃናት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ ፣ በቢሮው የማህበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ፣ በቢሮው የሴቶች ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ከተማ እንዲሁም የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሰመድ ሻሚል የተገኙ ሲሆን በተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርጉትን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments