የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እ...

image description
- In ሴቶች    1

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአመራሮች ስራ ርክክብ አከናወነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአመራሮች ስራ ርክክብ አከናወነ።

መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የቢሮው ኃላፊ በነበሩት በወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን እንዲሁም አዲስ ተሹመው በመጡት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ መካከል በዛሬው እለት የስራ ርክክብ ተደርጓል።

በመርሃ ግብሩም ላይ የቢሮው ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን በቢሮው በነበራቸው ቆይታ ከመንግስት አና ከፓርቲአቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር መስራታቸው እና በበርካታ ውጤቶችየታጀቡ ስራዎችን መስራታቸውን ገልፀው በቢሮ ለመጡ ውጤቶችና ስኬቶች አመራሩንና ሁሉንም ባለሙያዎች አመስግነዋል።

የስራ ኃላፊነታቸውንም በራሳቸው ተነሳሽነት እና ጥያቄ አቅራቢነት እንደለቁቁ ሆኖም የከተማችን የምክር ቤት አባል እንደመሆናቸው መጠን በከተማዋ የተለያዩ ተልዕኮዎች በቀጣይም የህዝብ ስራዎች በጋራ እንደሚሰሩገልፀዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም ቢሮው የሰራቸውን በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች እና እየተሰሩ ያሉትን፣ ጅምር ስራዎች እንዲሁም የቢሮው አሁናዊ ሁኔታ ገለፃ በማድረግ በቀጣይም ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር በጋራ በመተጋገዝ መከናወን ባለባቸዉ ተግባራት ላይም ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።

አዲስ የቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በበኩላቸው የቀድሞ የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን እንዲሁም ቢሮው ለሳዩዋቸው መልካም አቀባበል እና ቀና ትብብር አመስግነው ራሳቸውን እና የስራ ልምዳቸውን በሰፊው አስተዋውቀዋል።

አክለውም ቢሮው የሚሰራቸውን ስራዎች በበርካታ የስራ አጋጣሚዎች እንደሚረዱት ጠቅሰው በቀጣይም ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር በአንድ መንፈስ ተግባብተንና ተስማምተን በጥሩ የስራ መንፈስ ጥሩ ዉጤት ማምጣት እንደሚጠበቅ እና ለዚህም ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።

በተያያዘም በዕለቱ የቢሮው ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን የቢሮውን አመራር አባላት፣ የቢሮውን ጀነራል ካውንስል አባላት ፣ በቢሮው ስር የሚገኙ ተቋማት ስራ አስኪያጆችን እንዲሁም የቢሮው የ11ዱም ክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎችን አዲስ ተሹመው ለመጡት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አስተዋውቀው የተጀመሩ ስራዎችንም በጋራ ከግብ እንዲያደርሱ አደራ ብለዋል።

በዚህ የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የቢሮው ጀነራል ካውንስል አባላት ፣ በቢሮው ስር የሚገኙ ተቋማት ስራ አስኪያጆችን እንዲሁም የቢሮው የ11ዱም ክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎችን አዲስ ተሹመው ለመጡት የቢሮው ኃላፊ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments