የአዲስ አበባ ከተማ የሕፃናት ፓርላማ በዛሬው ዕ...

image description
- In የኽጻናት    0

የአዲስ አበባ ከተማ የሕፃናት ፓርላማ በዛሬው ዕለት መልሶ ተቋቋመ።

የአዲስ አበባ ከተማ የሕፃናት ፓርላማ በዛሬው ዕለት መልሶ ተቋቋመ።

መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

ቢሮው ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሆን የተወሰነው እና በከተማ ደረጃ የሚቋቋመውን የሕፃናት ፓርላማ በዛሬው እለት የምርጫ ስርዓቱን በጠበቀ እና በራሳቸው በሕፃናት ተሳታፊነት እና መራጭነት የፓርላማ ምስረታ ስነ-ስርዓቱን አከናውኗል።

በምስረታ ስነ-ስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የተገኙ ሲሆን ፓርላማው የህጻናትን ሁለንተናዊ መብቶችና ጥቅሞች ለማረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

አክለውም ፓርላማው የህጻናት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኝ ድምጽ መሆን የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው የህጻናት ፓርላማ እንዲጠናከር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

በቢሮው የሕጻናት ዘርፍ ም/ ቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ በመልዕክታቸው የህጻናት ፓርላማ መደራጀቱ ህጻናት ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎችን እንዲለማመዱ፣የውሳኔ ሰጪነት ሚናን እንዲያዳብሩ እንዲሁም ለመብቱ የሚሟገት ትውልድን እውን በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

አያይዘውም በከተማ ደረጃ ፓርላማውን ለማቋቋም በትምህርት ቤቶች፣ ክፍለ ከተማዎች እና ወረዳዎች አስፈላጊውን ሂደት ማለፉን አስረድተዋል።በዚህም በትምህርት ቤቶች ፣በወረዳዎች እና ክፍለ ከተማዎች መዋቅር የማደራጀት ስራ መከናወኑን ጠቁመዋል።

በምርጫ መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች በተገኙበት ከተመራጮች ትውውቅ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳን ያካተተ በታዛቢዎች የተፈተሸ የአፈ ጉባኤ፣ ምክትል አፈ ጉባኤና ጸሀፊ ምርጫ ተካሂዶ ውጤቱ ይፋ የተደረገ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴዎችንም የማደራጀት ስራ በእለቱ ተከናውኗል።

በእዚህም መሰረት በምርጫው አብላጫውን ድምፅ በማግኘት ታዳጊ እድላዊት ሀይሌ ካልዓይ ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሕጻናት ፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን የተመረጠች ሲሆን ፣ ታዳጊ ሲፈን ካሳሁን ከጉለሌ ክ/ከተማ ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሁም ታዳጊ ኢሳያስ በላይ ከለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፓርላማው ፀሀፊ በመሆን ተመርጠው ታማኝነታቸውንም በቃለ መሀላ አረጋግጠዋል።

በቢሮው የሕፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አንዱአለም ታፈሰ በበኩላቸው የሕፃናት ፓርላማ በተለያዩ ደረጃዎች ማለትምበወረዳዎች፣ በክ/ከተሞች፣ በከተማ፣ በት/ቤቶች እና በሕፃናትማሳደጊያ ማዕከላት ደረጃ ተቋቁሞ ሕፃናት መብቶቻቸውንመሠረት ያደረጉ ተሳትፎዎችና ልምምዶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ይሄንኑም ከወረዳ እስከ ከተማ ያለውን የሕፃናት ፓርላማ መዋቅርመልሶ በማጠናከርና በማደራጀት ሂደት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት

፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ ለኤፊድሪ እምባ ጠባቂ እንዲሁም ለቀድሞ የሕፃናት ፓርላማ አባላት በቢሮው ስም የምስጋናና የእውቅና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

በቀጣይም ቢሮው በዛሬው እለት የተቋቋመው የሕጻናት ፓርላማ ህፃናት ከትምህርታቸዉ ጎን ለጎን የፓርላማ ምንነትን እንዲያውቁ እና ከቀድሞ የሕጻናት ፓርላማ አባላት ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር፣ በቢሮው የሕጻናት ዘርፍ ም/ ቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬን ጨምሮ የአዲስ አበባ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ተማሪዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በምርጫ ስርዓቱ ከተለያዩ የከተማዋ ትምህርት ቤቶች ፣በወረዳዎች እና ክፍለ ከተማዎች ተውጣጥተው የተሳተፉ ተማሪዎች የሕጻናት ፓርላማ በመቋቋሙ መደሰታቸውን ገልፀው በእለቱም ህጻናት ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎችን እንዲለማመዱ በር መከፈቱን ጠቁመዋል።

በተለይም በእለቱ ከቂርቆስ ክ/ከተማ በመጣው በታዳጊ በጌታ ቀኙ አማካኝነት በቀረበው እና የሕፃናት ጥቃትን ለመጠቆም በሚያስችለው የዌብሳይት መተግበሪያ ለበለጠ ስራ መነሳሳታቸውን እና በቀጣይም በራሳቸው በመተማመን መብታቸውን እና ደህንነታቸውን ለማስከበር ከፓርላማው ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments