ቢሮው አግልግሎት እና ተደራሽነቱን በተመለከተ ከ...

image description
- In ሴቶች    2

ቢሮው አግልግሎት እና ተደራሽነቱን በተመለከተ ከሚዲያ አካላት ጋር የምክክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን አከናውኗል።

ቢሮው አግልግሎት እና ተደራሽነቱን በተመለከተ ከሚዲያ አካላት ጋር የምክክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን አከናውኗል።

መጋቢት 05 ቀን 2017 ዓ.ም አ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ

ቢሮው የመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ማህበራዊ ችግሮችን በመከላከል የህፃናት፣ የሴቶች፣ የአረጋዊያን እና የአካል ጉዳተኞች መብትና ደህንነት ተጠብቆ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የእኩል እድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ክፍሎች ካሉበት አስከፊ ህይወት እንዲወጡ የማብቃት ስልትን መሰረት በማድረግ በማሸጋገር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት እንዲሁም ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሚዲያ አካላት ጋር በቅርበት ይሰራል።

በዛሬውም እለት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚዲያ ድርሻ የላቀ ነው በሚል መሪ ሀሳብ ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር የምክክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን አከናውኗል።

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስጀመሩት የቢሮው አማካሪ ዶ/ር ታደለ ደመኮ ቢሮው የሚከውናቸው በርካታ ሰው ተኮር ተግባራቶቹ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚነካ በተለይም ሴቶችን የሚያበቃ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶችን በሁሉም በኩል ለማብቃት በሚደረጉ ጥረቶች አይነተኛ አስተዋፅኦ ያለው ነው ብለዋል።

በቢሮው የሚከናዎኑ ተግባራት ፓሊሲዎች እና የሚዲያ ሚና ምን እንደሚመስል የገለፁት በቢሮው የሴቶች ተሳትፎ ማብቃትና ተጠቃሚነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስፍራሽ አልማው ሲሆኑ ቢሮው በተለያዩ ፕሮግራሞቹ በተለይም በጤናዉ ዘርፍ ሴቶችን ግንዛቤ መስጠት ለቤተሰብ፣ ለህብረተሰብ እንዲሁም ለሀገር ጤናማ ማህበረሰብን ከመፍጠር አንፃር ከ75,000 በላይ ሴቶችን በተለያዩ የስነተዋልዶ ትምህርቶች እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ፣

እንዲሁም ከ25,000 በላይ ሴቶችን በተለያዩ የልማት ህብረት አደረጃጀቶች በማቀፍ በልዩ ልዩ ተጠቃሚነታቸውን በሚያጎሉ ተግባራት ማሳተፉ ቢሮው በትኩረት የሚሰራቸውን ስራዎች ከብዙ በጥቂቱ ማሳያ መሆናቸውን ገልፀው ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ማብቃት የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ ሚዲያዎች እገዛችሁ አይለየን ሲሉም አሳስበዋል።

በቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሐድጉ ፀሃየ በበኩላቸው ቢሮው የሚሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተደራሽ ለማድረግ የሚዲያውን አይነተኛ አስተዋፅኦ ቢሮው የሚያምንበት መሆኑን እና ይህንኑ የጋራ ሀላፊነታችንን እንዴት እንወጣ የሚለውን ለመመካከር እና የጋራ ተግባቦት ላይ ለመድረስ ያለመ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

በእለቱ በተለያዩ አይነት የሚዲያ ዘርፎች የሚሰሩ የሚዲያ አካላት እና የሶሻል ሚዲያ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በመድረኩም ስለቢሮው አግልግሎቶች ግንዛቤ እንዳገኙበት የገለፁ ሲሆን ይህንኑም በበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በምን መልኩ እንስራ በሚል ውይይት በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments