እኩል እድል እና አካታች ትምህርት ለሁሉም!
እኩል እድል እና አካታች ትምህርት ለሁሉም!
የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ለማክበርና ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በተለያዩ ጊዜያት ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍና ሃገር አቀፍ የህግ ማዕቀፎች ወጥተዋል።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የከተማ አስተዳደሩ ሃገራችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ቻርተሮች መሰረት ማንኛውም ልማት አካል ጉዳተኞችን ያማከል ወይም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆናቸው ክትትል በማድረግ መሬት ላይ ተጨባጭ ለውጦች እንዲመጡ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑን የገለፁ ሲሆን
አክለውም በተለይም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ተቋቁመው ውጤታማ መሆናቸው የሚያስመሰግን በመሆኑ ለሌሎች አርአያ በሚሆኑበት አግባብ ማበረታታት ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ አካል ጉዳተኞች ውክልና እና ተሳትፎ ለማሳደግ ቢሮው የሚያግዝና የሚያስተባብር መሆኑን በመጥቀስ በዕለቱ እውቅናና ሽልማት ለበቁ ተማሪዎች እስካሁን ያካበቱትን ልምድ በተጨማሪ ቁርጠኝነት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በቢሮው የማሕበራዊ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው አካል ጉዳተኞችን ያላካተተ ተግባራት እንደ ሀገር ውጤታማ እንደማያደርጉን በማመን መንግስት በተለይም ቢሮው የአካል ጉዳተኞች ተሳታፊና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን በተለይም በልዩ ፕሮግራም ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎችን ዕውቅና እና ሽልማት በመስጠት የአካል ጉዳተኞች አካቶ ትምህርት እንዲጠናከር አካል ጉዳተኝነት ከትምህርትና ከስኬት እንደማያስቀር ውጤት በማምጣት ለስኬት መድረስ እንደሚቻል አላማ ያደረግ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀው ተማሪዎቹ ከዕውቅና ባሻገር ስኬታማ ዜጋ ይሆኑ ዘንድ ተጨማሪ ኃላፊነት የሚቀበሉበት ዝግጅት መሆኑን በማብራራት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክ አስተላልፈዋል፡፡
በዕለቱ ከሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማሕበር፣ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ተወክለው የመጡ አካላት በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ አስተማሪ ተሞክሯቸውን ያካፈሉ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተኛ ወስደው ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲ ለሚገቡ 40 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 2 ሚሊዬን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ተሸላሚ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆችም ለእውቅና እና ሽልማቱ ቢሮውን በማመስገን ለበለጠ ትጋት እንዳነሳሳቸውም ገልፀዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም የአ.አ.ሴ.ህ.ማ.ጉ.ቢሮ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments